በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“አገራዊው ምርጫ በሁሉም አካባቢዎች ይካሄዳል” - አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ


አቶ ታገሰ ጫፎ እና ወ/ሮ ሊያ ካሳ
አቶ ታገሰ ጫፎ እና ወ/ሮ ሊያ ካሳ

“አገራዊው ምርጫው በ2013 ዓ.ም እንዲካሄድ” ሲል ፓርላማው ያስተላለፈው ውሳኔ “በሕገወጥ መንግሥት እንዲተገበረ የታቀደ እና ተቀባይነት የሌለው ነው” ሲል የትግራይ ክልል ተቃወመው። አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው፤ በፌደሬሽን ምክር ቤት የሥልጣን ዕድሜው የተራዘመለት ሕጋዊ መንግሥት እንዳለ በመግለፅ ፤“በእልህና በስሜታዊነት ተነሳስቶ ያልተገባ ነገር መናገር ተገቢ አይለምም” ብለዋል።

በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክኒያት በኢትዮጵያ የታወጀውና ለአምስት ወራት ያህል ተፈፃሚ ሲሆን የቆየው አስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ነሐሴ 30/2012 ዓ.ም ማብቃቱን ተከትሎ የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ባለፈው ሳምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክረ ሐሳብ አቅርበው ነበር።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የቀረበው ምክረ ሐሳብ ለኮሮናቫይረስ መከላከያ ጥንቃቄዎች እየተደረጉ በዚያውም፤ “በምን መልኩ የማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ እንችላለን?” ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ ምክረ ሐሳብ መቅረቡን ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

ምክር ቤቱም ይህን ምክረ ሐሳብ ካደመጠ በኋላ፤ በሴቶች ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ እና የሕግ፣ የፍትሕ እና ዴሞክራሲ ጉዳያዮች ቋሚ ኮሚቴዎች አማካኝነት የውሳኔ ሐሳብ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።

ከእነዚህ ውሳኔዎች ውስጥ ምክር ቤት ስድስተኛ ሃገራዊ ምርጫ እንዲካሄድ ያስተለላፈው ውሳኔ፤ በ“ሕገወጥ መንግሥት እንዲተገበረ የታቀደ እና ተቀባይነት የሌለው ነው” ሲል የትግራይ ክልል መንግስት ተቃውሞውን አሰምቷል።

የክልሉን መንግስት ተቃውሞ በተመለከተ የኮሙዩኒኬሽን ሃላፊ ወይዘሮ ሊያ ካሳ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግሥት ሕጋዊነቱ ከመስከረም 25 በኋላ ስለሚያበቃ ቅቡልነት ያለው ምርጫ ለማካሄድ ባለአደራ መንግስት መቋቋም አለበት ብለዋል።

ከዚሁ የትግራይ ክልል መግለጫ ጋር በተያያዘ ጥያቄ የቀረበላቸው የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በፌደሬሽን ምክር ቤት የሥልጣን ዕድሜው የተራዘመለት ሕጋዊ መንግሥት እና ሕጋዊ ተቋማት ያሏት ታላቅ አገር ናት - ኢትዮጵያ ብለዋል።

(ጽዮን ግርማና ሙሉጌታ አፅብሐ ያጠናቀሩትን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

“አገራዊው ምርጫ በሁሉም አካባቢዎች ይካሄዳል” - አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:50 0:00


XS
SM
MD
LG