በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትግራይ አቃብያነ ሕግ የክልሉን መንግሥት በዳኝነት ጉዳዮች፤ በጣልቃ ገብነት ይከሳሉ


መቀሌ
መቀሌ

“ለረዥም ጊዜ ስናቀርበው የነበረ የደመወዝና የጥቅማጥቅም ጥያቄ የክልሉ መንግሥት ምላሽ ሳይሰጠው ቆይቷል” ሲሉ ትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ አቃብያነ ሕግ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት ቅሬታቸውን ገልፀዋል።

በክልል ደረጃም ነፃ የሆነ የጠቅላይ አቃቤ ሕግ ተቋም ሊቋቋም እንደሚገባ አሳስበዋል።

በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጡ የክልሉ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋ የደመወዝና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄን ለመፍታት ለክልሉ መንግሥት የመክፈል አቅም የሚከብድ መሆኑን ጠቁመው ጉዳዩ ግን “ለመንግሥት ቀርቦ እየታየ ነው” ብለዋል።

ነፃ ተቋምን አስመልክቶም የፍትህ ቢሮ የመንግሥት አካል መሆኑን አስታውሰው “በግልፅ ለመንግሥትና ለህዝብ ወግኖ የሚሠራ ተቋም ነው” ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

የትግራይ አቃብያነ ሕግ የክልሉን መንግሥት በዳኝነት ጉዳዮች፤ በጣልቃ ገብነት ይከሳሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:24 0:00


XS
SM
MD
LG