በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ክልል በተፈናቃዮች በተያዙ ትምህርት ቤቶች 200ሺሕ ተማሪዎች እየተማሩ እንዳልኾነ ተገለጸ

በትግራይ ክልል በተፈናቃዮች በተያዙ ትምህርት ቤቶች 200ሺሕ ተማሪዎች እየተማሩ እንዳልኾነ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:26 0:00

በትግራይ ክልል በተፈናቃዮች በተያዙ ትምህርት ቤቶች 200ሺሕ ተማሪዎች እየተማሩ እንዳልኾነ ተገለጸ

በትግራይ ክልል፣ 110 ትምህርት ቤቶች በተፈናቃዮች መጠለያነት እያገለገሉ እንደኾኑ የጠቀሰው የክልሉ ትምህርት ቢሮ፣ በትምህርት ቤቶቹ መማር የሚገባቸው 200ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ውጭ ኾነው እንደሚገኙ ገልጿል፡፡

ተፈናቃዮቹን ወደ ቀዬአቸው በመመለስና የወደሙ የትምህርት መሣሪያዎችን በመተካት፣ የመማር ማስተማር ሒደቱን ማስቀጠል እንደሚገባ፣ የቢሮው ሓላፊ ዶክተር ኪሮስ ጒዕሽ ተናግረዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ(UN-OCHA) ባወጣው ሪፖርት ደግሞ፣ በክልሉ 106 ትምህርት ቤቶች በተፈናቃዮች እንደተያዙ ገልጾ፣ በዚኽም ምክንያት፣ 163 ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ውጭ እንደኾኑ አመልክቷል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG