በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ክልል ተዋጊዎችን በማሰናበት ወደ ኅብረተሰቡ የማዋሐድ ሥራ ተጀምሯል


በትግራይ ክልል ተዋጊዎችን በማሰናበት ወደ ኅብረተሰቡ የማዋሐድ ሥራ ተጀምሯል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:50 0:00

በትግራይ ክልል ተዋጊዎችን በማሰናበት ወደ ኅብረተሰቡ የማዋሐድ ሥራ ተጀምሯል

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ፥ 17 ቢሊዮን ብር በላይ የቀጣይ ዓመት በጀት አጽድቋል

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ በፕሪቶርያው ስምምነት መሠረት፣ በጦርነቱ የተሳተፉ ተዋጊዎችን በማሰናበት ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለስ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

በያዝነው ሳምንት፣ 50 ሺሕ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎች እንደተሰናበቱ፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ተናግረዋል፡፡

ይኸው፣ ተዋጊዎችን የማሰናበት እና ከማኅበረሰቡ ጋራ የማዋሐድ ሒደት፣ በየጊዜው እንደሚቀጥል፣ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡

በሌላ ዜና፣ የክልሉ የጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ፣ 2016 በጀት ዓመት የሚውል፣ 17 ነጥብ 3 ቢልዮን ብር አጽድቋል፡፡

የክልሉ ፕላን ኮሚሽን ኮምሽነር ሓንሳ ተኽላይ፣ ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለጹት፣ የጸደቀው በጀት፣ 2013 .. በአንድ ቢልዮን ብር ያነሰና ከክልሉም ፍላጎት አንጻር አነስተኛ እንደኾነ አመልክተዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG