በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ክልል ተዋጊዎችን በማሰናበት ወደ ኅብረተሰቡ የማዋሐድ ሥራ ተጀምሯል


በትግራይ ክልል ተዋጊዎችን በማሰናበት ወደ ኅብረተሰቡ የማዋሐድ ሥራ ተጀምሯል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:50 0:00

• የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ፥ ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ የቀጣይ ዓመት በጀት አጽድቋል

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ በፕሪቶርያው ስምምነት መሠረት፣ በጦርነቱ የተሳተፉ ተዋጊዎችን በማሰናበት ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለስ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

በያዝነው ሳምንት፣ ከ50 ሺሕ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎች እንደተሰናበቱ፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ተናግረዋል፡፡

ይኸው፣ ተዋጊዎችን የማሰናበት እና ከማኅበረሰቡ ጋራ የማዋሐድ ሒደት፣ በየጊዜው እንደሚቀጥል፣ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡

በሌላ ዜና፣ የክልሉ የጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ፣ ለ2016 በጀት ዓመት የሚውል፣ 17 ነጥብ 3 ቢልዮን ብር አጽድቋል፡፡

የክልሉ ፕላን ኮሚሽን ኮምሽነር ሓንሳ ተኽላይ፣ ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለጹት፣ የጸደቀው በጀት፣ ከ2013 ዓ.ም. በአንድ ቢልዮን ብር ያነሰና ከክልሉም ፍላጎት አንጻር አነስተኛ እንደኾነ አመልክተዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG