በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ክልል በሰውም ሆነ በእንስሳት ላይ ያጋጠመ ድርቅ የለም ተባለ

በትግራይ ክልል በሰውና በእንስሳት ያጋጠመ ድርቅ እንደሌለና ለመጭው ክረምት ዝግጅት እየተከናወኑ እንደሚገኙ የክልሉ የእርሻና የገጠር ልማት ቢሮ አሳውቋል፡፡

በትግራይ ክልል በሰውና በእንስሳት ያጋጠመ ድርቅ እንደሌለና ለመጭው ክረምት ዝግጅት እየተከናወኑ እንደሚገኙ የክልሉ የእርሻና የገጠር ልማት ቢሮ አሳውቋል፡፡ በሌላ በኩል እየተቀያየረ ባለው የተፈጥሮ የአየር ሁኔታ ምክንያት ዘንድሮ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገሮች ላይ የተምች ወረርሽኝ ሊከሰት እንደሚችል ከወዲሁ ተሰግቷል፡፡ በደቡብ ኢትዮጵያ ገና ከአሁኑ ታይቷል፡፡

ከዚህም በመነሳት ገበሬዎች ማሣችውን በጥንቃቄ በፈተሽ ያገኙት መረጃ በፍጥነት ለባለሞያዎች ማሳወቅ እንደሚኖርባቸው ማሣሰቢያ ተሰጥቷል፡፡

በትግራይ ክልል በአለፈው ክረምት ጥሩ ዝናብ በመዝነቡ ምክንያት አርሶ አደሩ ጥሩ ምርት ማግኘቱን የትግራይ ክልል የእርሻና የገጠር ልማት ቢሮ ግምገማ ይገልፃል፡፡

ገበሬው ከክረምቱ ዝናብ ብቻ ሳይሆን በመስኖ ማልማትን፣ በቂ ውሃ ማግኘት መቻሉንም ቢሮው ያስረዳል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በትግራይ ክልል በሰውም ሆነ በእንስሳት ላይ ያጋጠመ ድርቅ የለም ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:45 0:00

  • 16x9 Image

    ግርማይ ገብሩ

This item is part of

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG