በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ሱዳን መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከባድ የምግብ እጥረት እየጠበቃቸው ነው


ለሁለት ዓመታት ያህል ግጭት ሲካሄድበት በቆየው ደቡብ ሱዳን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከባድ የምግብ እጥረት እየጠበቃቸው እንደሆነና ረሀብም ሊከሰት እንደሚችል በመግለጽ አለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስጠንቅቋል።

ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በደቡብ ሱዳን ያለው የመራብ ሁኔታ ከፍተኛ በመሆኑ የሚያሳሰብ እንደሆነ ጠቁሟል። ብዙ ሰዎች ደግሞ ህክምና ያስፈልጋቸዋል። ብዙ የሃገሪቱ ነዋሪዎች ሁለቱን አመታት በምግብና በህክምና ፈለጋ እንዲሁም ከጦርነቱና ከወሲብ ጥቃት ለመራቅ ሲንከራተቱ እንዳሳለፉት ስዊትዘርላንድ ያለው የሰብአዊ መብት ድርጅት አስገንዝቧል።

ደቡብ ሱዳን ውስጥ በመንግስትና በአማጽያን ሃይሎች መካከል በሚካሄደው ግጭት ምክንያት በቀላሉ በማይደረስባቸው አከባቢዎች 1.7 ሚልዮን የሚሆኑ ሰዎች ከመኖርያቸው እንደተፈናቀሉ፣ ብዙዎች ተደብቀው እንደሚኖሩ በደቡብ ሱዳን የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ስራ አስተባባሪ ፍሎረንስ ጂለት (Florence Gillette) ገልጸዋል።

“በየጫካውና በደሴቶች ይደበቃሉ። አንዳንዴም ከጥቃት ርቀው በሚገኙ ክፍት ደሴቶች ይሰፍራሉ። እነዚህ ሰዎች ታድያ ፍርሀት ስላደረባቸው ወደ አከባቢያቸው ለመመለስ አይፈልጉም” ብለዋል።

ፍሎረንስ ግለት (Florence Gillett) እንደሚሉት አለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴና ሌሎች የረድኤት ድርጅቶች አልፎ አልፎ ለተፈናቃዮቹ የምግብ እርዳታ ሊያቀርቡ ይችላሉ። ይሁንና በቂ እርድታ አያገኙም። ብዙዎቹ ደግሞ ከጫካና ከመስኮች ሊያገኙት በሚችሉ የሚበላ ነገር እንደሚኖሩ ፍሎረንስ ግለት (Florence Gillett) ገልጸዋል።

ዘጋብያችን ሊሳ ሽላይን የድርጅቱ ዋና ጽህፈት ቤት ከሚገኝበት ጄኔቫ የላከችውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ አቅርበዋለች። ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

በደቡብ ሱዳን መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከባድ የምግብ እጥረት እየጠበቃቸው ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:45 0:00

XS
SM
MD
LG