በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከአቢ ላቀው እና ከጸደንያ ገ/ማርቆስ ጋራ ስለ "ኮራ" ቆይታ አድርገናል


ቴዲ አፍሮ እና አቢ ላቀው
ቴዲ አፍሮ እና አቢ ላቀው

ከ54 አፍሪካ አገራት ለሚሳፉበት የዘንድሮው የአፍሪካውያን የሙዚቃ (Kora) ውድድር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቲዲ አፍሮ) በዝነኛ ድምጻዊ (Legendary Award) ዘርፍ እንዲሁም በሴት ምርጥ የባህል ሙዚቃ (Best Traditional Music Artist) አርቲስት አቢ ላቀው እጩ ኾነዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ከአንዷ እጩ አቢ ላቀው እና ቀደም ሲል ይህን ሽልማት ካገነችው ከጸደንያ ገ/ማርቆስ ጋራ ቆይታ አድርገናል፡፡

አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቲዲ አፍሮ) እና አርቲስት አቢ ላቀው በየዓመቱ ለሚካሄደው አፍሪካውያን የሙዚቃ ውድድር (Kora) ሽልማት እጩ ኾነዋል፡፡ ኮራ ከተመሰረተበት ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ ዐሥራ ሁለት ጊዜ ውድድሮች ተካሂደዋል፡፡ ዐስሩ ውድድር የተካሄደው በደቡብ አፍሪካ ሲሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት በቡርኪናፋሶ እና በኮትዲቩዋር ተካሂዷል፡፡ የዘንደሮው ደግሞ መጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም በናሚቢያ ይካሄዳል፡፡ ከ54 አፍሪካ አገራት ለሚሳፉበት የዘንድሮው ውድድር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቲዲ አፍሮ) በዝነኛ ድምጻዊ (Legendary Award) ዘርፍ እንዲሁም በሴት ምርጥ የባህል ሙዚቃ /Best Traditional Music Artist/ አርቲስት አቢ ላቀው እጩ ኾነዋል፡፡ አቢ ላቀው እጩ የኾነችበት ሥራዋ የኔ ሃበሻ የተሰኝ የሙዚቃ ክሊፕ ሲሆን ዩቲዩብ ላይ በዛሬው ዕለት 7.2 ተመልካች አግኝቷል፡፡

ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች በኮራ ውድድር ሲታጩ የመጀመሪያቸው አይደለም፡፡ ጸደንያ ገብረ ማርቆስ፣ሸዋንዳኝ ኃይሉ፣ ቴዎድሮስ ሞሲሳ ፣አሁን በሕይወት የሌለችው ሚኪያ በኃይሉ እንዲሁም ከዲያስፖራ ኢትዮጵያዊ ሃዴ ኃይሌ እጩ ነበሩ፡፡ ከእነዚህ እጩዎች መካከልም በ2004 ዓ.ም ድምጻዊት ጸደንያ ገብረ ማርቆስ አሸናፊ ኾናለች፡፡ ይህንኑ በተመለከት ባልደረባችን ጽዮን ግርማ አቢ ላቀው ጋር ስልክ ደውላ… ለውድድር የተመረጠውን ዘፈን አሰማቻት…..ከዛስ…. ቀሪውን ከተያያዘው ድምፅ ማድመጥ ትችላላችሁ፡፡

በተጨማሪም ጽዮን ግርማ ድምጻዊት ጸደንያ ገብረማርቆስን አነጋግራታለች፡፡ የኮራ የሙዚቃ ውድድር ምን እንደሆን ጽዮን ላቀረበችላት ጥያቄ ጸደንያ ምላሽ በመስጠት ትጀምራለች፡፡

ለቴዲ አፍሮ እና ለቢ ላቀው መልካም ዕድል እንመኛለን፡፡ ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ድምፅ ያድምጡ፡፡

ከአቢ ላቀው እና ከጸደንያ ገ/ማርቆስ ጋራ ስለ "ኮራ" ቆይታ አድርገናል
please wait

No media source currently available

0:00 0:20:30 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG