በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከ2 ሺህ በላይ የደምሕት አባላት ወደ አገር እንደሚገቡ ተገለፀ

ከ2 ሺህ በላይ የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ (ደምሕት) ሠራዊት አባላት፣ በቅርብ ጊዜ ወደ አገር ውስጥ ይገባሉ ሲሉ፣ የንቅናቄው ሊቀ መንበር አቶ መኮነን ተስፋይ ተናገሩ።

ከ2 ሺህ በላይ የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ (ደምሕት) ሠራዊት አባላት፣ በቅርብ ጊዜ ወደ አገር ውስጥ ይገባሉ ሲሉ፣ የንቅናቄው ሊቀ መንበር አቶ መኮነን ተስፋይ ተናገሩ።

የንቅናቄው አመራሮች በዛሬው ዕለት ወደ መቀሌ ከተማ ሲገቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። አቶ መኮነን እንደተናገሩት የደምሕት አባላት ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለማመቻቸት፣ ከመንግሥት ጋር ተነጋግረናል ብለዋል።

በአቀባበሉ የተገኙ የትግራይ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሐላፊ አቶ ነጋ በርኸ በበኩላቸው፤ የክልሉ መንግሥትና ገዢው ፓርቲ ህወሓት፤ ከደምሕት ጋር በሚያገናኛቸው ጉዳዮች አብረው ይሰራሉም ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

ከ2 ሺህ በላይ የደምሕት አባላት ወደ አገር እንደሚገቡ ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:22 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG