ሰሜናዊ ታንዛኒያ ውስጥ በደረሰው ከባድ የጎርፍ መጥለቅለቅ እና ናዳ የተነሳ ቢያንስ 47 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 85 ሰዎች መቁሰላቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናገሩ፡፡
ትናንት ሰኞ ሌሊቱን የጣለው ዝናብ ሃናንግ ወረዳ ውስጥ መኪናዎችን ጨምሮ በንብረት ላይ መጠነ ሰፊ ውድመት አድርሷል፡፡
የታንዛኒያ መንግሥት በሀገሪቱ በአያሌ ዓመታት ከደረሱት ሁሉ የከፋ በተባለው የጎርፍ እና የመሬት መናድ አደጋ የተጠመዱትን ብዙ መቶ ነዋሪዎች እንዲረዳ የጦር ሠራዊቱን አሰማርቷል፡፡
ዱባይ ላይ እየተካሄደ ባለው የተመድ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ የሚገኙት የታንዛኒያ ፕሬዚደንት ሳሚያ ሱሁሉ በጎርፉ አደጋ ምክንያት አቋርጠው ወደሀገራቸው እንደሚመለሱ አስታውቀዋል፡፡
ኢትዮጵያን፡ ኬኒያን፡ ሶማሊያን እና ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ ሌሎችም የምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች ኤል ኒኞ በሚባለው የአየር ሁናቴ በተባባሱ የጎርፍ አደጋዎች የተጠቁ ሲሆን ብዙ መቶ ሰዎች ሞተዋል፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡
መድረክ / ፎረም