ዋሺንግተን ዲሲ —
በምዕራብ ጉጂና ጌዴዖ ዞኖች ግጭት ቀዬውን ጥሎ እንዲበተን የተገደደው ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ ዛሬም ደራሽ ዕርዳታ ይሻል።
ለግጭቶቹ ዘላቂ መፍትሔና ተፈናቃዩን ሕዝብ መልሶ ለማቋቋም የአካባቢውና የፌድራል መንግስት ሊወስዱ ከሚገቡ እርምጃዎች ባሻገር ዜጎች በሕይወት አድኑም ሆነ በሃገር ደረጃ ብጥብጥን በሚያርቁና ሰላም በሚያመጡ ጥረቶች ዜጎች ያላቸውን ሁነኛ ድርሻ የሚያመላክት ምግባር ነው።
የዋሽንተን ዲሲው “ዓለምቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት” የተሰኘው የጋራ ግብረ-ኃይል መሰንበቻውን ለጌድዎ ተፈናቃዮች እርዳታ አሰባስቧል።
ከግብረ ኃይሉ ሊቀ መንበር ከአርቲስት ታማኝ በየነ ጋር የተካሄደውን ቃለ ምልልስ ሁለተኛ ክፍል ከዚህ ያድምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ