በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ውድ ዋጋ ይከፍላሉ…” - ፕሬዚዳንት ትረምፕ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት በካቢኔአቸው ስብሰባ ላይ ተቀምጠው የሶሪያን የኬሚካል ጥቃት ጉዳይ እየመከሩ ሳሉ /ሰኞ፤ ሚያዝያ 1 / 2010 ዓ.ም. - ዋሺንግተን ዲሲ/
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት በካቢኔአቸው ስብሰባ ላይ ተቀምጠው የሶሪያን የኬሚካል ጥቃት ጉዳይ እየመከሩ ሳሉ /ሰኞ፤ ሚያዝያ 1 / 2010 ዓ.ም. - ዋሺንግተን ዲሲ/

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን፣ ሃገራቸው ሩሲያና ኢራን ከትናንት በስተያ ቅዳሜ የሶሪያዋ ዱማ ከተማ ላይ ለተፈፀመው የኬሚካል ጥቃት “ተጠያቂ ናቸው” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ክሥ አሰምተዋል።

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን፣ ሃገራቸው ሩሲያና ኢራን ከትናንት በስተያ ቅዳሜ ምሽት የሶሪያዋ ዱማ ከተማ ላይ ለተፈፀመው የኬሚካል ጥቃት “ተጠያቂ ናቸው” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ክሥ አሰምተዋል።

በጥቃቱ ቢያንስ አርባ ሰው መገደሉን የሶሪያ የመብቶች ተሟጋቾችና የሕክምና ተቋማት ምንጮች ገልፀዋል።

“በክሎሪን ጋዝ የተፈፀመ ነው” የተባለው ጥቃት መድረሱ የተሰማው የሶሪያ መንግሥት የእሥላም ሠራዊት ከሚባለው አማፂ ቡድን ጋር ጀምሮት የነበረው ድርድር ከፈረሰ በኋላ ቡድኑ በዋና ከተማዪቱ ደማስቆ አጠገብ ይዟቸው የነበሩ አካባቢዎችን ለማስለቀቅ የሃገሪቱ ጦር የማጥቃት ዘመቻ በከፈተበት ወቅት ነው።

የጥቃቱ መፈፀም እንደተሰማ የአሜሪካው ፕሬዚዳት ባወጧቸው የትዊተር መልዕክቶች “እንስሣው” በሚል የዘለፋ ቅፅል ለጠሯቸው የሶሪያ ፕሬዚዳንት ባሻር አል አሳድ “ድጋፍ እየሰጡና እየተከላከሉላቸው ወታደሮቻው እንዲህ ዓይነቱን አረመኔያዊ አድራጎት እንዲፈፀሙ የልብ ልብ የሰጧቸው ሩሲያና ኢራን ናቸው” ብለዋል።

ሶሪያና ሩሲያ ተፈፅሟል የተባለውን የኬሚካል ጥቃት አስተባብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

“ውድ ዋጋ ይከፍላሉ…” - ፕሬዚዳንት ትረምፕ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:33 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG