በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜንና ደቡብ ሱዳን ድንበራቸውን በጋራ ለመጠበቅ ተስማሙ


በስምምነቱ መሠረት በጋራ ቅኝት የሚያደርጉትን ከወታደር ነፃ ክልል፥ ዓለምአቀፍ አካል ይቆጣጠራል

በአንድ የአዲስ አበባ ሆቴል ውስጥ ለሦስት ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ ትላንት ማታ የተደረሰውን የሴኪዩሪቲ ስምምነት የፈረሙት፥ አንጋፋ የሰሜንና ደቡብ ሱዳን ወታደራዊ አዛዦች ናቸው።

በሱዳን ጉዳይ የአፍሪቃ ህብረት ልዩ ጓድ መሪ በቀድሞው የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዘዳንት Thabo Mbeki ሸምጋይነት የተደረሰው ይህ ስምምነት፥ የሁለቱ ወገኖች ከፍተኛ ባለሥልጣናት በየጊዜው እየተገናኙ የፀጥታውን ጉዳይ የሚከታተሉበትን መንገድ ያመቻቻል።

ለአዲስ አበባው የሰላም ንግግር ቅርበት ያላቸው ዲፕሎማቶች እንደሚሉት፥ ኢትዮጵያ በሰሜኑና ደቡቡ ኃይሎች መካከል በግጭት ተከላካይነት የሚያገለግሉና ከወታደር ነፃ የሆነውን ክልል የሚቆጣጠሩ ወታደሮቿን ወደ ድንበሩ ለመላክ ፈቃደኝነቷን ገልጻለች። የተ መ ድ የፀጥታው ምክር ቤትም ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያ የሆኑ የሰላም አስከባሪ ወታደሮችን ለመመደብ የቀረበውን ዕቅድ ሊቀበል እንደሚችል ይገለጻል።

ዝርዝሩን ከዚህ ያድምጡ።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG