በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር ከ8 እስከ 75 ዕድሜ ባላቸው ሰለባዎች ላይ ወሲባዊ ጥቃት ፈጽሟል - ተመድ


ፎቶ ፋይል - የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (RSF)
ፎቶ ፋይል - የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (RSF)

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (RSF) እና አጋር በሆኑ የአረብ ሚሊሻዎች ከ18 ወራት በላይ በዘለቀው ጦርነት ከስምንት እስከ 75 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ንፁሀን ዜጎች ላይ “ዘግናኝ” የሆነ ጾታዊ ጥቃት ፈጽመዋል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተልእኮ ዘገባ አመልክቷል።

ዛሬ ማክሰኞ የወጣው የመንግሥታቱ ድርጅት ተልእኮ ዘገባ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎቹና አጋሮቹ ሰለማዊ ዜጎችን በመድፈር እና አንዳንዶቹን ሴቶች በመጥለፍ የወሲብ ባሪያ ማድረጋቸውን አስታውቋል፡፡

ዘገባው አክሎም “ጾታዊ ጥቃት ሰላማዊ ዜጎችን ለማሸበር እና ከጠላት አንጃዎች ጋር ግንኙነት ያላቸውን ለመቅጣት እንደ ስልት ጥቅም ላይ ይውላል” ብሏል፡፡

የተልእኮው ሊቀ መንበር መሀመድ ቻንዴ ኦትማን ከተጎጂዎች፣ ቤተሰቦች እና ምስክሮች ጋራ የተደረገ ቃለ ምልልስ መሰረት ባደረገው ለባለ 80 ገጹ ዘገባ በሰጡት መግለጫ "በሱዳን የመዘገብነው ከፍተኛ የፆታዊ ጥቃት መጠን በጣም አስገራሚ ነው" ብለዋል።

ሪፖርቱ በግጭቱ ውስጥ የተንሰራፋውን ጾታዊ ጥቃትን በተመለከተ “ሮይተርስ እና የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ያደረጉትን ምርመራ አጎልቶ የሚያሳይ ነው” ሲል የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።

ከሱዳን ጦር ጋራ እየተዋጋ የሚገኘው የፈጥኖ ደራሹ ጦር ከሮይተርስ ለቀረበለት ጥያቄ ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጠም፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ ቀደም የተባለውን ክስ አጣርቶ ወንጀለኞችን ለህግ እንደሚያቀርብ ማስታወቁ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG