በሱዳን የፍጥኖ ደራሽ ኃይሉ ባደረሰው ጥቃት በአንድ ከተማ ብቻ ከ120 በላይ ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀረ አንድ የሐኪሞች ቡድን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቀዋል።
ኃይሉ በመካከለኛው ምሥራቅ ሱዳን የነበረውን የበላይነት በሱዳን ሠራዊት መነጠቁን ተከትሎ ለተከታታይ ቀናት በሲቪሎች ላይ ተኩስ መክፈቱን እንዲሁም ሴቶችን እና ልጃገረዶችን አስገድዶ መድፈሩን ተመድ አስታውቋል።
ኃይሉ ባለፈው ሳምንት ለስድስት ቀናት ሳሪሃ በተባለች ከተማ ባደረሰው ጥቃት ቢያንስ 124 ሰዎች እንደተገደሉና ከ200 በላይ የሚሆኑት ደግሞ እንደቆሰሉ የሱዳን የዶክተሮች ኅብረት አስታውቋል።
ታምቡል በተባለች ከተማ በደረሰው ጥቃት ደግሞ ከ46ሺሕ 500 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የበርካቶችን ሕይወት በመቅጠፍ ላይ ያለው ጦርነት በተለይም በሴቶችና ሕፃናት ላይ የከፋ ስቃይ ማድረሱን ድርጅቱ ጨምሮ አስታውቋል።
መድረክ / ፎረም