በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን ተፋላሚዎች ልዑካን ስለሰብአዊ ረድኤት ሊነጋገሩ ሳዑዲ አረቢያ ገቡ


ሁለቱ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች መልዕክተኞች፣ የሰብአዊ ረድኤት መተላለፊያን ስለ መክፈት አስመልክቶ ሊነጋገሩ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተጉዘዋል፡፡
ሁለቱ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች መልዕክተኞች፣ የሰብአዊ ረድኤት መተላለፊያን ስለ መክፈት አስመልክቶ ሊነጋገሩ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተጉዘዋል፡፡

ሁለቱ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች መልዕክተኞች፣ የሰብአዊ ረድኤት መተላለፊያን ስለ መክፈት አስመልክቶ ሊነጋገሩ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተጉዘዋል፡፡

የሁለቱም ወገኖች መልዕክተኞች፣ “የምንገኛኘው፥ የሰብአዊ ረድኤት ኹናቴውን ቀለል ለማድረግ ስለሚቻልበት መንገድ ለመነጋገር እንጂ፣ ውጊያውን ስለማቆም ለመደራደር አይደለም፤” ሲሉ በአጽንዖት አስታውቀዋል፡፡

የቅድመ ድርድሩ ውይይት፣ ባለፈው ቅዳሜ ተጀምሯል፡፡ ሳዑዲ አረቢያ፣ 100 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ሰብአዊ ርዳታ እንደምትልክ አስቀድማ ቃል ገብታለች፡፡

በሱዳን የጦር ሠራዊት እና በፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ኃይሉ መካከል፣ እ.አ.አ. ባለፈው ሚያዝያ 15 ቀን ውጊያው ከተቀሰቀሰ ወዲህ፣ በብዙ መቶ ሺሕዎች የተቆጠሩ ሰዎች ከቀዬአቸው ተፈናቅለዋል፡፡ ብዙዎቹ ወደ አጎራባች ሀገራት ተሰድደዋል፡፡

በጀነራል አብዱል ፈታሕ አል ቡርሃን የሚመራው የሀገሪቱ የጦር ሠራዊት እና በጀነራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ የሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል፣ ውጊያው ከተጀመረ ወዲህ ለንግግር ተቀምጠው አያውቁም፡፡ በየጊዜው ያደረጓቸው የተኩስ አቁም ስምምነቶችም፣ ጦርነቱን ማስቆም ቀርቶ ጋብ ሊያደርጉት አልቻሉም፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የፍልሰተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር በቅርቡ እንዳስታወቀው፣ ውጊያው ቢያንስ 334ሺሕ ነዋሪዎችን ለአገር ውስጥ ተፈናቃይነት ሲዳርግ፣ 100ሺሕ ሱዳናውያን ደግሞ ከሀገር ውጭ ተሰድደዋል፡፡ በይቀጥላልም፣ ከ800ሺሕ የሚበልጡ ሱዳናውያን ሀገር ጥለው ሊሰደዱ እንደሚችሉ፣ የፍልሰተኞች ኮሚሽነሩ አስጠንቅቋል፡፡

በጸጥታ ችግር የተነሣ፣ አብዛኛው የሰብአዊ ተራድኦ እንቅስቃሴ ተቋርጧል ወይም ተቀዛቅዟል፡፡ በርካታ የረድኤት ሠራተኞችም በውጊያው ተገድለዋል፡፡ የርዳታ እህል ምዝበራም፣ የሰብአዊ ተራድኦ እንቅስቃሴዎችን የሚያስተጓጉል ሌላው ችግር መኾኑ ተዘግቧል፡፡

የዓለም የምግብ ፕሮግራም፥ ከ13 እስከ 14 ሚሊዮን ዶላር ግምት ያለው፣ ወደ 17 ሺሕ ቶን የሚጠጋ ምግብ፣ በሀገሪቱ ከሚገኙ መጋዘኖቹ መሰረቁን አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG