በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስና የመረጃ ሰብሳቢ ሠራተኞች ውዝግብ


የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ
የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ

ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ለሚያሠራው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ካርታ ሥራ ያሰማራቸው ቡድኖች አባላት ላለፉት ሁለት ወራት ከስምምነታችን ውጭ በሆነ ሁኔታ ደመወዝም አበልም አልተከፈለንም ሲሉ ቅሬታ አሰሙ።

ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ለሚያሠራው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ካርታ ሥራ ያሰማራቸው ቡድኖች አባላት ላለፉት ሁለት ወራት ከስምምነታችን ውጭ በሆነ ሁኔታ ደመወዝም አበልም አልተከፈለንም ሲሉ ቅሬታ አሰሙ።

የሁለት የቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ኃላፊዎች ጉዳዩ ያልተዘጋና በእንጥልጥል ያለ መሆኑን በመግለፅ የየራሣቸውን መልሶች ሰጥተዋል።

ኤጀንሲው በመላ ሃገሪቱ ያሰማራው እያንዳንዳቸው ስድስት ወይም ሰባት ሠራተኞች የነበሩባቸውን 180 ቡድኖች ሲሆን እነዚህ ከአንድ ሺህ በላይ ባለሙያዎች ላለፈው አንድ ዓመት ተኩል ለሚሆን ጊዜ መረጃዎችን ሲያሰባስቡና ሲያቀናጁ ቆይተዋል።

ትግራይ ውስጥ በተለያዩ አባባቢዎች ተሠማርተው ከነበሩ ቡድኖች የአንዱ አባላት ሃድላት ክፍለከተማ ፍርድ ቤት ክሥ መሥርተው ችሎቱ ባለፈው ሰኞ፤ ነኀሴ 22/2009 ዓ.ም ውሣኔ ሊሰጥ ቀጥሯል።

በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ አበባ ውስጥም ተሠማርተው የነበሩ ቡድኖች ተመሣሣይ ችግር እንደገጠማቸው ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ከስምምነታችን ውጭ አበላችን ተቋርጦብናል የሚሉት ሁሉም የ180ዎቹም ቡድኖች አባላት ከሆኑና መሥሪያ ቤቱም ለመክፈል ከወሰነ መንግሥት ከአራት ሚሊየን ብር ያላነሰ የኋላ ክፍያ እንዲፈፅም ይጠበቅበታል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስና የመረጃ ሰብሳቢ ሠራተኞች ውዝግብ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:04 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG