በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባራክ ኦባማ ትላንት ማታ ስለሀገሪቱ ሁኔታ የሚገመግመውን ሰባተኛውንና የመጨረሻውን አመታዊ ንግግር አድርገዋል


የዩናይትድ ስቴስ ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ ትላንት ማታ ስለሀገሪቱ ሁኔታ የሚገመግመውን ሰባተኛውንና የመጨረሻውን አመታዊ ንግግር አድርገዋል። ፕረዚዳንቱ በህግ መምርያና በህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት ፊት ቀርበው ባደረጉት ንግግር ስለመጪው አመት ብቻ ሳይሆን ስለቀጣዩቹ አምስት አመታትና ከዚያም ርቀው እንዲመልከቱ አስገንዝበዋል።

ፕረዚዳንት ኦባማ ስለ ሀገሪቱ ሁኔታ ባደረጉት የመጨረሻው ንግግራቸው ተስፋን አንጸባርቀዋል። ሀገሪቱ ካለምንም ብዥታ በእውነታ ላይ የተመሰረት አመለካከት ያላት፣ ደግነትና ለጋስነት የማይለያት በአሁኑ ወቅት ደግሞ የአሸባሪነት ስጋት ያለባት ሀገር እንደሆነች ገልጸዋል።

“በአሜሪካ ላይ ስትነሱ እኛም እንመጣባችኋለን።”

አሸባሪዎቹ በፓሪስና በካሊፎርኒያ ጥቃት ያደረሱ ቢሆንም አገር በቀልና የውጭ ሀገራት አሸባሪዎች አደገኛነት እንዳለ ሆኖ የሀገራችንን ህልውና አደጋ ላይ የመጣል ብቃት የላቸውም ብለዋል ፕረዚዳንት ኦባማ። ያም ሆኖ ግን የሪፑብሊካውያን የበላይነት የሰፈነበት ምክር ቤት እርmጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርበዋል።

“ይህ ምክር ቤት ይህን ጦርነት ስለማሸነፍ ጉዳይ አክብዶ የሚያይ ከሆነ ለወታደሮቻችንና

ለመላው አለም መልእክት የማስተላለፍ ፍላጎት ካለው እስላማዊ መንግስት ነኝ በሚለው ጽንፈኛ ቡድን ላይ ወታደራዊ ሃይል ለመጠቀም መፍቀድ ይኖርበታል። በጉዳዩ ላይ ድምጽ መስጠት ይገባዋል።”

ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ሰባተኛውንና የመጨረሻውን ንግግራቸውን ትናንት ማታ ለአሜሪካ ሕዝብ አሰምተዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:26 0:00

ፕረዚዳንት ኦባማ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት በኩባ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳም ጠይቀዋል። ፓሲፊክን በሚመለከት ደግሞ ምክር ቤቱ የትራንስ ፓሲፊክ አጋርነት የንግድ ስምምነትን እንዲያጸድቅ ጥያቄ አቅርቧል።

ፕረዚዳንት ኦባማ ስለ አሜሪካ ሁኔታ የሚገመግመው ንግግራቸውን ከማሰማታቸው በፊት በሁለት የአከባቢ ጥበቃ ጀልባዎች ላይ የነበሩ 10 አሜሪካውያን መርከበኞች በኢራን ታስረዋል። በኢራን ጉዳይ ላይ ጥርጥሪ የሚያንጸባርቀውን ምክር ቤት ከኢራን ጋር የተደረገውን የኑክሌር ስምምነት ለማሳመን በወተወቱበት ውቅት እንኳን ስለታሰሩት መርከብኞች አላነሱም።

“ኢራን በአሁኑ ወቅት የኑክሌር ፕሮግራምዋን ጋብ አድርጋለች። የዩረንየም ክምችትዋን አርቃለች። አለም በዚህ መልክ ሌላ ጦርነትን አስወግዷል።”

የደቡብ ካሮላይና ክፍለ ግዛት አስተዳዳሪ Nikki Haley በበኩላቸው ለፕረዚዳንት ኦባማ ንግግር የሪፑብሊካውያን ምላሽ ላይ የተመሰረተ ንግግር አድርገዋል። የዋይት ሃውስ ቤተ-መንግስት በተለየ አስተዳደር ላይ ሲሆን ያላቸውን ራእይ አንጸባርቀዋል።

“እኛ የምናደርገው አለም አቀፍ ስምምነት በተቃራኒው ሳይሆን እስራኤል የምትደሰትበት

ኢራን ግን የምትቃወመው ይሆና።”

የህዝብን ድምጽ በመከታተል ተግባር ላይ የተሰማሩት ሩፑብሊካዊ Matt Gammon ፕረዚዳንት ኦባማ ስላቀረብዋቸው ጥያቄዎች አቛማቸውን ገልጸዋል።

“ካቀረብዋቸው ጥያቄዎች አንዳቸውም ቢሆኑ በተለይም በዚህ ምክር ቤት ከባድ እርምጃ ይወሰዳል ብለው የሚጠብቁ አይመስለኝም። ስላነስዋቸው ነጥቦች እንደሚቆረቆሩ ለህዝቡ ለማሳየት ይመስለኛል። ለወደፊት በሚታውሱበት ታሪክም ይመዘገባል።”

ፕረዚዳንት ኦባማ ትላንት ማታ ባደረጉት ሃገሪቱ ስለምትገኝበት ሁኔታ የሚገልጸው ንግግር ዩናይትድ ስቴትስ በፖለቲካ አመለካከት መከፋፈል መቀጠልዋ እንደሚያሳዝናቸው ገልጸዋል።

ሆኖም ሪፑብሊካውያን የሚያሰሙትን አሉታዊ ንግግርንም ነቅፈዋል።

“ስለአሜሪካ ኢኮኖሚ መዳከም የሚነገረው ነገር ሁል ባዶና የተጋነኑ የፖለቲካ ቃላት ናቸው።”

ሪፑብሊካዊው ፕረዚዳንታዊ ተወዳዳሪ ዶናልድ ትራምፕ የፕረዚዳንት ኦባማን ንግግር ህይወት አልባ የሆነ ደካማ ንግግር ብለዋታል። ሌላው ሪፑብሊካዊ ተወዳዳሪ ቴድ ክሩዝ ደግሞ ስለ ሀገሪቱ ሁኔታ የሚገልጽ ሳይሆን “ሁኔታውን የሚያስተባብል” ነው ብለዋል።

ፕረዚዳንት ኦባማ ባደረጉት ንግግር ለማስተላለፍ የፈልጉት የፖለቲካ መልእክት አሜሪካውያን የሪፑብሊካውያንን ልፈፋ ችላ በማለት የወደፊቱን ትውልድ በሚመለከቱ

ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩሩ ማሳመን ነው።

የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ Carolyn Presutti ያጠናቀረችውን ዘገባ አዳንች ፍሰሀየ አቅርባዋለች።

ባራክ ኦባማ ትላንት ማታ ስለሀገሪቱ ሁኔታ የሚገመግመውን ሰባተኛውንና የመጨረሻውን አመታዊ ንግግር አድርገዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:33 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG