በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ስለ ዶ/ር መረራ መታሠር


ማርክ ቶነር፤ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ምክትል ቃል አቀባይ /ፎቶ ፋይል/
ማርክ ቶነር፤ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ምክትል ቃል አቀባይ /ፎቶ ፋይል/

በዶ/ር መረራ ጉዲና መታሠር ላይ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ምክትል ቃል አቀባይ ማርክ ቶነር ለጋዜጠኞች ዛሬ የሰጡት መግለጫ በቪኦኤ የአፍሪካ ቀንድ አገልግሎት የአማርኛ ዝግጅት ክፍል እንደሚከተለው ተተርጉሟል፡፡

“የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር የሆኑት ዶክተር መረራ ጉዲና በኢትዮጵያ መንግሥት መታሠራቸውን ሰምተናል፡፡ ዘገባው አሳስቦናል፡፡ መንግሥቱ በዶክተር መረራ ላይ ያለውን ማንኛውንም ክሥ ለሕዝብ እንዲያሳውቅ በፅኑ እናበረታታለን፡፡ የመታሠራቸው ነገር እውነት ከሆነ አድራጎቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ነፃ ድምፆችን ለማፈን የሚጣሉት ገደቦች እየተጠናከሩ ለመምጣታቸው አንድ ተጨማሪ ማሳያ ነው የሚሆነው፤ በግልፅ ለመናገር ደግሞ ኢትዮጵያ ያወጀችው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ምናልባት ተቃውሞን ዝም ለማስባልና በሕገመንግሥት የተረጋገጡ የኢትዮጵያን ዜጎች መብቶች ለመንፈግ ጉዳይ እየዋለ ለመሆኑ ያለንን ሃሣብ ይበልጥ ያጠናክረዋል፡፡ ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ባወጣ ጊዜ የፖለቲካ ለውጦችን እወስዳለሁ ሲል የገባውን ቃል የሚፃረር ነው፡፡ ስለዚህ ጉዳዩን በቅርብ እንከታተለዋለን፡፡”

ሚስተር ማርክ ቶናር የሰጡትን መግለጫ ሙሉ ቃል ከታች ከተያያዙት የቪድዮና የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ስለ ዶ/ር መረራ መታሠር
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:28 0:00

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ስለ ዶ/ር መረራ መታሠር
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:52 0:00

XS
SM
MD
LG