በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛው ኢትዮጵያ ናቸው


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ስታተርፊልድ
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ስታተርፊልድ

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ስታተርፊልድ መጋቢት 12 እና 13 ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት ባለሥልጣናት፣ እንዲሁም ከረድኤት ድርጅት ተወካዮች ጋር ለመነጋገር ወደ ኢትዮጵያ መጓዛቸውን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

ልዩ መልዕክተኛው በትናንትናው ዕለት ከአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ከኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ጋር እንዲሁም ከአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደህንነት ኮሚሽነር ጋር፣ ሱዳንና ኢትዮጵያን ጨምሮ፣ በአካባቢው ጉዳዮች መነጋገራቸውን መግለጫው አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG