በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከን ከአዲሱ የአፍሪካ ቀንድ መልዕክተኛ ጋር ለመስራት መዘጋጀታቸውን ገለጹ


ፎቶ ፋይል፦ አምባሳደር ዴቪድ ስታተርፊልድ
ፎቶ ፋይል፦ አምባሳደር ዴቪድ ስታተርፊልድ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ሰሞኑን ከኃላፊነታ እየተነሱ በሚገኙት አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ምትክ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ዴቪድ ስታተርፊልድ ጋር አብሬ ለመስራት በጉጉት እየተጠባበቅኩ ነው ሲሉ አስታወቁ፡፡

ብሊንከን ባወጡት መግለጫ "አምባሳደር ፊልት ማን ባለፈው ዓመት መጀመሪያ ላይ ይህን ኃላፊነት እንዲወስዱ የጠየቅናቸው ዓመት ላልሞላ ጊዜ ነበር" ብለዋል፡፡

“ይሁን እንጂ በአፍሪካ ቀንድ የቀጠለው አለመረጋጋትና እርስ በርሱ የተሳሰረው የፖለቲካ፣ የደህንነትና ሰብዓዊ ተግዳሮት፣ ዩናይትድ ስቴትስ ቋሚ የሆነ ትኩረት እንድትሰጥ ጠይቋታል” ብለዋል፡፡

ከአትላንቲክ ካውንስል የአፍሪካ ሴንተር ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ካሜሮን ኸድሰን ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያና በሱዳን ያሉ ቀውሶች ተሳታፊ በሆኑ ወገኖች ላይ ጫና ለመፍጠርና በቀጠናው ሰላም ለማስፈን ቋሚ ልኡካንን መመደብ የሚገባት መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ ከአሜሪካ ድምጹ ዘጋቢ መቩንጋኔ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንዲህ ብለዋል

"ለዚህ ነገር ትኩረት መስጠታቸው ትክክለኛ ነገር ይመስለኛል፡፡ ምክያንቱም ያልተጠናቀቁ ብዙ ሥራዎች አሉ፡፡ እናም ደግሞ ተስፋ አደርጋለሁ በቀጠናው በአግባቡ የተወከሉ ዲፕሎማቶች የሌሉን መሆኑን የተገነዘብን ይመስለኛል፡፡ ዛሬ በሶማሊያ አምባሳደር የለንም፡፡ በሱዳን አምባሳደር የለንም፡፡ ስለዚህ በአምባደር ደረጀ የተወከለ ሰው እዚያ አገር ውስጥ ከሌለህ፣ በተለይ በአፍሪካ ቀንድ፣ አሁን ያሉት ዓይነት ቀውሶች ባሉበት ሁኔታ፣ ያለምንም ጥርጥር አንድ የሆነ ልኡክ የሚያስፈልግህ ይመስለኛል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምባሳደሩ ኃላፊነቱን ለመረከብ ያሳዩትን ፈቃደኝነት አድንቀው 9 ወራት ያገለገሉት አምባሳደር ፌልትማን በአማካሪ ደረጀ ሚኒስቴሩን እሳቸውን በማማከር እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡

ብሊንከን በቀጠናው ከገጠሙን ፈተናዎችና ካገኘናቸው እድሎች አንጻር እንደዚህ ዓይነት ከፍተኛ ባለሙያዎች ያሉን በመሆናችን እድለኞ ነን ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG