በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስትር በሀዋሳ ከተማ


የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስትር በሀዋሳ ከተማ በነበረው የክልሉ ወጣቶች የሰላምና ሀገር ግንባታ ኮንፈረንስ ላይ ልዩነቶችንና ብዘሃነትን ስለማናስተናግድ ሰላማችንን እያጣን ነው አሉ፡፡

የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስትር በሀዋሳ ከተማ በነበረው የክልሉ ወጣቶች የሰላምና ሀገር ግንባታ ኮንፈረንስ ላይ ልዩነቶችንና ብዘሃነትን ስለማናስተናግድ ሰላማችንን እያጣን ነው አሉ፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ "ደኢህዴን" የህዝቦችን ጥቅም የሚያስከብርበት ቁመና ላይ ይደርሳል እንጂ እንደሚባለው አይፈርስም ብለዋል፡፡

ድርጅቱ የአደረጃጀትና የማንነት ጥያቄዎችን ህዝቦች ተወያይተው ስለራሳቸው እንዲወስኑ ያመቻቻል እንጂ ያለህዝብ ፍላጎት ውሳኔ እንደማያስተላልፍ ተናግረዋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በበኩላቸው በክልሉ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የዴሞክራሲያዊ ባህል ማሳደግና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የወጣቱን ጥያቄ በማፈንና የተለያዩ አስተሳሰቦች እንዳያራመዱ ማድረግ የትም እንደማያደርሰን ካለፈው ጉዞአችን አረጋግጠናል ነው ያሉት፡፡

ከክልሉ የተወጣጡ ወጣቶች በሰላምና አገር ግንባታ ሂደት ዙርያ ትናንትና ከትናንት በስቲያ በሃዋሳ ከተማ የመከሩበት መርሃግብር ተጠናቋል፡፡ ዮናታን ዘብዴዎስ ከሃዋሳ፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስትር በሀዋሳ ከተማ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:32 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG