በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ስፍራ በተነሳ ግጭት ሰዎች ተገደሉ

በደቡብ ክልል ቡርጂ ወረዳና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን አዋሳኝ አምስት የቡርጂ ወረዳ አርሶ አደሮች በታጠቁ የኦነግ አባላት ሲገደሉ፤ ሊሎች ሰባት ሲቪሎች ደግሞ የመቁሰል አደጋ እንደረሰባቸው የቡርጂ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

በደቡብ ክልል ቡርጂ ወረዳና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን አዋሳኝ አምስት የቡርጂ ወረዳ አርሶ አደሮች በታጠቁ የኦነግ አባላት ሲገደሉ፤ ሊሎች ሰባት ሲቪሎች ደግሞ የመቁሰል አደጋ እንደረሰባቸው የቡርጂ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የቡርጂ ተወላጆች በሚደርስባቸው ማንነታቸውን መሠረት ያደረገ ጥቃት ሳቢያ ከቡሌ ሆራ፣ ከተል ተሌና ሞያሌ በመፈናቀል ላይ መሆናቸውን የአካባቢው ተወላጆችና ተጎጂዎች ይናገራሉ፡፡

በተጨማሪም ለረሃብ መጋለጣቸውን ያመለከቱት ተፈናቃዮች ከመንግሥትም ሆነ ከሌሊሎች ደራሽ ሰብዓዊ ዕርዳታ አላገኘንም ይላሉ።

በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ዞን አስተዳደር በበኩሉ የአስተዳደር ወሰንና የሃብት “ይገባኛል” ጥያቄዎች ለግጭቶቹ መንሰኤ መሆናቸውን ገልጦ፤ በአከባቢው የታጠቀ ኃይል ስለመኖሩ ግን መረጃ የለኝም ችግሩን ለመፍታትም የአካባቢዎቹን ሕዝብ ለማገናኘት ጥረት እየተደረገ ነው ብሏል፡፡

ዮናታን ዘብዴዎስ ዝርዝሩን አድርሶናል።

በደቡብና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ስፍራ በተነሳ ግጭት ሰዎች ተገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:56 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG