ሃዋሳ —
በሃሳብ የበላይነት የሚያምንና ምክንያታዊ ወጣት መፍጠር ባለመቻሉ ሀገሪቱ ለአለመረጋጋትና ስጋት ተዳርጋለች አሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ ወጣቶች ሊግ አባላት፡፡
ወጣቶቹ የሚጠቅመንን በመለየት ለሰላም ዘብ የሚንቆምበት ወቅት አሁን ነው ብለዋል፡፡ "ምክንያታዊ ወጣት ለሁለንተናዊ ለውጥ" በሚል መርህ ሀሳብ ለለሶስት ቀናት የሚካሄደው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ "ዴኢህዴን" ወጣቶች ሊግ 4ተኛው መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተከፍቷል፡፡
ጉባኤው በወጣቶች ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ዙርያ ይመክራል፡፡ ወጣቶች በአገሪቱ የታየውን ለውጥ በባለቤትነት በምን መልክ ማስቀጠል እንደሚችሉ አቅጣጫ ያስቀምጣልም ተብሏል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ