ዋሺንግተን ዲሲ —
በአለፈው ሃምሌ ወር የደቡብ ሱዳን መዲና ጁባ አዲስ ውጊያ ከተካሄደ በኋላ በሀገሪቱ ግጭት ሲጨምር ቆይቷል፡፡
በድቡብ ሱዳን ያለው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተልዕኮ በውጊያው ወቅት ሲቪሎችን ለመጠበቅ ተገቢ እርምጃ አልወሰደም በማለትም የዓለምቀፍ ማህበረሰብ ሲነቅፍ ቆይቷል፡፡
ጁባ ውስጥ የፀጥታ ሁኔታ ተሻሽሎ እንደሆነ በማጤን የድርጅቱ ተልዕኮ አካል የሆነው የኢትዮጵያ ክፍል ጥበቃ በሚያደርግበት አካባቢ የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ጂልክሬክ አብራ ተዘዋውራ ካየች በኋላ የላከችው ዘገባ አለ አዳነች ፍስሃዮ ታቀርባለች፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡