በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞች እየተወነጃጀሉ ነው


የደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንት ሳልቫኪር እና የተቃዋሚዎች መሪ ሪያክ ማቻር እአአ 2014
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንት ሳልቫኪር እና የተቃዋሚዎች መሪ ሪያክ ማቻር እአአ 2014

የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመም በኋላ ቢሆን “የተኩስ አቁሙ እየተከበረ አይደለም” ሲሉ የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ መሪ ሪያክ ማቻር ተናግረዋል። የደቡብ ሱዳን መንግሥት ጦር አዛዥ ጄነራል ጆንሰን ጁማ በበኩላቸው ሰላማዊ ዜጎችን በመጥለፍ በማቻር የሚመሩ ያሏቸውን ሽማቂዎች ከስሰዋል።

የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚዎች መሪ ሪያክ ማቻር ተኩስ ማቆሙ ያልተከበረው የሰላም ስምምነቱ ከፈረመበት አንስቶ መሆኑን ገልፀው “ተኩስ በቋሚነት ለማቆም ስምምነት ከተደረሰበትና ይህም በይፋ ከተነገረበትም ጊዜ ጀምሮ ቢሆን ጦርነቱ ኢኳቶሪያ ግዛት ውስጥ እንደቀጠለ ነው” ብለዋል።

በራዲዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ ኢኳቶሪያ ግዛት ውስጥ ሰላማዊ ዜጎችን በመጥለፍ ተቃዋሚ ሸማቂዎችን ከሰዋል።

የደቡብ ሱዳን ጦር አዛዥ ጄነራል ጆንሰን ጁማ በበኩላቸው ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል “በሪያክ የሚመራው የደቡብ ሱዳን ሕዝብ ነፃ አውጭ ሠራዊት ላለፉት ሁለት ወራት ዜጎችን የማገት ወንጀል ላይ ሰማርቷል” ብለዋል፡፡

ሃምሣ የሚሆኑት ሰዎችን ማስለቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ፡፡

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞች እየተወነጃጀሉ ነው /ርዝመት - 3ደ05ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:05 0:00

XS
SM
MD
LG