በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን የእርስ-በእርስ ውጊያና የኮንጎ ሥጋት


"ከስምንታችን መሃከል አንድ እርሡ ወንድሜ ብቻ ነው የታሰረው። እንደሚመስለኝ ወንድሜ ተዋጊ ወታደር መስሏቸው ይሆናል። ነገር ግን እርሱ ተዋጊ ወታደር አይደለም።" ግሬስ ገበ ቁጥሩ 30 ሺህ የሚደርስ ስደተኛ በማስተናገድ ላይ በምትገኘው የድንበር ከተማ አባ ከተጠለሉ ደቡብ ሱዳናውያን አንዷ።

"ከስምንታችን መሃከል አንድ እርሡ ወንድሜ ብቻ ነው የታሰረው። እንደሚመስለኝ ወንድሜ ተዋጊ ወታደር መስሏቸው ይሆናል። ነገር ግን እርሱ ተዋጊ ወታደር አይደለም።" ግሬስ ገበ ቁጥሩ 30 ሺህ የሚደርስ ስደተኛ በማስተናገድ ላይ በምትገኘው የድንበር ከተማ አባ ከተጠለሉ ደቡብ ሱዳናውያን አንዷ።

“አንዳንዶች ቀድሞ የነበራቸውን የተዋጊነት ማንነታቸውን ጥለው በስደተኝነት መቀጠል ሲመርጡ፤ ሌሎች ደግሞ ቆይተው ወደ መጡበት በመመለስ በውጊያው ለመሳተፍ ያቅዳሉ። ማን በእርግጥ ውጊያውን እርግፍ አድርጎ ለመተው እንደወሰነ፤ ማንኛው ደግሞ አገግሞና ራሱን አጠናክሮ፣ ለውጊያው ለመሰናዳት እንደመጣ መለየት በእጅጉ አዳጋች ነው።” Alan Boswell የስደተኞች ጉዳይ አጥኚ።

የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፑብሊክ፤ የሚበዙት የደቡብ ሱዳን አማጽያን ሳይሆኑ እንዳልቀሩ የተጠረጠሩ ድንበሯን አቋርጠው በመጉረፍ ላይ የሚገኙ ስደተኞች ሁኔታ የከሰተውን ለመቋቋም ብርቱ ጥረት ይዛለች።

የጦር ሠራዊቷ በበኩሉ እስካሁን ዘጠኝ ያህል ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ይፋ ተደርጓል። የቤተሰብ አባላቶቻቸው ግን “የተያዙት ሰዎች፤ ተራ ስደተኞች እንጂ የአማጽያን ቡድኑ አባላት አይደሉም” ሲሉ እንዲለቀቁላቸው እየጠየቁ ነው።

የደቡብ ሱዳን መንግስት በአንድ የአገሪቱ ደቡብ ምዕራብ ግዛት የሚገኝ የአማጽያኑ የጦር ካምፕ ከተቆጣጠረበት ካለፈው ሳምንት አንስቶ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች አካባቢውን ጥለው ወደ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፑብሊክ በመፍለስ ላይ ናቸው።

ከእነኚህም ውስጥ አንዳንዶቹ የአማጽያኑ ሚሊሻዎች በመሆናቸው፤ ግጭቱ ድንበር ተሻግሮ እንዳይቀጥል የሰጋችው ኮንጎ ታዲያ በአማጽያኑ ተዋጊነትና ጀሌነት የጠረጠረቻቸውን በማሰር ላይ ነች። ስደተኛ አባላቱ ግን የተያዙት ወጣቶች በምኑም የሌሉበት ናቸው እያሉ ነው።

የደቡብ ሱዳን የእርስ በእርስ ውጊያ በቀጠለበት፤ የኮንጎም ፈተና፤ ከደቡብ ሱዳን በሚያዋስናት ድንበራሯ ከሁለት ወገኑ ተዋጊዎች ጉዳይ ጋር የተያያዘው ግብ-ግቧ ቀጣይነት አይቀሬ ነው።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የደቡብ ሱዳን የእርስ-በእርስ ውጊያና የኮንጎ ሥጋት
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:27 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG