በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ያቀረቡት የጋራ ክልል ምስረታ ጉዳይ


ሀዋሳ
ሀዋሳ

የኢትዮጵያ 11ኛው ክልል ሊሆን ይችላል የተባለ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ በአንድነት ክልል ለመመስረት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያቀረቡት ጥያቄ በሙሉ ድምጽ ጸደቀ።
አምስተኛ ዙር የፓርላማ ዘመን ስድስተኛ ዓመት አንደኛ መደበኛ ጉባኤ በማካሄድ ላይ ያለው የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ላቀረቡት የጋራ ክልል ምስረታ ጥያቄ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈጻሚነት ውሳኔ ህዝበ እንዲደራጅ የቀረበውንም የውሳኔ ሀሳብ ወስኗል፡፡
ቪኦኤ ያነጋገራቸው ጥያቄውን ያቀረቡ የዞኖች ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች፣ ነዋሪዎች እና የህዝብ ተወካዮች ለዘመናት ሲጠይቁት የቆየ ህገ መግሥታዊ ጥያቄያቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ መልስ ያገኛል ብለው እንዳልጠበቁ ተናግረዋል።
የአካባቢው ህዝብ ከዚህ በፊት ይድረስበት የነበረው የእክሉነት፣ የመልካም አስተዳደር፥ የልማትና የፍትሃዊነት ችግር የሚቀረፋል እምነት እንዳሳደረባቸውም ገልጠዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ያቀረቡት የጋራ ክልል ምስረታ ጉዳይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:18 0:00


XS
SM
MD
LG