በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጎርፍ ሙላት በተዋጡ የዳሰነች ወረዳ ት/ቤቶች “ሦስት ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ታጉለዋል”

በጎርፍ ሙላት በተዋጡ የዳሰነች ወረዳ ት/ቤቶች “ሦስት ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ታጉለዋል”
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:12 0:00

በጎርፍ ሙላት በተዋጡ የዳሰነች ወረዳ ት/ቤቶች “ሦስት ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ታጉለዋል”

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ፣ በኦሞ ወንዝ ጎርፍ የተጥለቀለቁት ትምህርት ቤቶች በሙላቱ በመዋጣቸው፣ ከሦስት ሺሕ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ እንደኾኑ፣ የወረዳው አስተዳደር እና የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ ተናገሩ።

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ፍቅረ ማርያም አይመላ፣ በጎርፍ ሙላቱ በተዋጡት ትምህርት ቤቶች ምትክ፣ ተፈናቃዮች በተጠለሉባቸው ስፍራዎች ጊዜያዊ ትምህርት ቤቶችን ለማቋቋም እንቅስቃሴ እንደተጀመረ አስታውቀዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበርያ ቢሮ(UN-OCHA)፣ በወረዳው የሚገኙ 28 ትምህርት ቤቶች በውኃ ሙላቱ በመጎዳታቸው የመማር ማስተማር ሒደቱ እንደተስጓጎለና የጤና ተቋማትም ከአገልግሎት ውጭ እንደኾኑ አረጋግጧል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG