በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
በደቡብ ክልል ለተፈጠረው ግጭት የወረዳና የዞን አመራሮች ኃላፊነታቸውን እንዲለቁ ተነገራቸው

በደቡብ ክልል ለተፈጠረው ግጭት የወረዳና የዞን አመራሮች ኃላፊነታቸውን እንዲለቁ ተነገራቸው


የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ

ባለፈው ሳምንት ግጭት በተቀሰቀሰባቸውና በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት በደረሰባቸው ሦስት የደቡብ ክልል ከተሞች የሚገኙ የወረዳና የዞን አመራሮች ኃላፊነት ወስደው ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው ሊለቁ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ተናገሩ።

በደቡብ ክልል ለተፈጠረው ግጭት የወረዳና የዞን አመራሮች ኃላፊነታቸውን እንዲለቁ ተነገራቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:47 0:00

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ ማምሻውን ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋራ ባደረጉት ውይይት በሦስቱ ከተሞች የዞኑም ሆነ የወረዳው ኃላፊዎች ለደረሰው ጉዳት ኃላፊነት ወስደው ከሥልጣናቸው እንዲለቁ ጠይቀዋል።

የሲዳማ ማኅበረሰብ የፊቼ ጨምበላላ ዘመን መለወጫ በዓል ዋዜማ በሀዋሳ ከተማ ባለፈው ማክሰኞ ሲከበርና ሰኞ ዕለት በወልቂጤ ከተማ በኳስ ጨዋታ ቡድን ደጋፊዎች መካከል በተነሳው ፀብ በተፈጠረው ግጭት ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።

በዚህም በሀዋሳ፣ በወላይታ ሶዶና በወልቂጤ የ15 ስዎች ሕይወት ማለፉ፣ ወደ መቶ የሚጠጉ ሰዎች የቆሰሉ ንብረት የወደመ፣ ነዋሪዎችም የተፈናቀሉ ሲሆን፤ ግጭቱን ተከትሎ የአሜሪካ ድምፅ በወቅቱ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ግጭቶቹ በከተማዎቹ በሚነገርና በሚሰራጨው የተጋነኑ የቁጥር መረጃዎች ተባብሰው እንደነበር፣ በእነዚህ መረጃዎችም “የእኔ ብሔር እዛ እየተጠቃ፤ እኔ ለምን ዝም አላለሁ?” በሚል ተነሳሽነት ለከፍተኛ ፀብና ጥፋት እንዲጋበዙ ማድረጉን ነዋሪዎቹን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

ጉዳቶቹ በደረሱበት አካባቢዎች ሁኔታውን የሚያበርድ የፀጥታ ኃይል እንዳልነበር የዐይን እማኝ ነኝ ያሉ ነዋሪዎችን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ባደረጉት በዚህ ውይይት ላይ ፤ “የፖለቲካ ነጋዴ የሆናችሁ ካድሬዎች ምንም ፖለቲካ ብትነግዱ ሲደመር ትርፉ ዜሮ የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ ስለማይሆን ፖለቲካ እየነገዳችሁ ሺሕ ዓመት እንደማይኖር አውቃችሁ ተሰብሰቡ " - ሲሉ መክረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG