በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ሱዳን ውስጥ የተጠራው የተቃዋሞ ሰልፍ አልተካሄደም


ፎቶ ፋይል፦ ጁባ ከተማ
ፎቶ ፋይል፦ ጁባ ከተማ

በደቡብ ሱዳን ትናንት ሰኞ ሊካሄድ ተጠርቶ የነበረው የመንግሥት ተቃዋሚ ሰልፍ ሳይሳካ ቀርቷል።

ዋና ከተማዋ ጁባ ውስጥ ብዛት ያላቸው የጸጥታ ኃይሎች ጎዳናዎች ላይ ተሰማርተው የዋሉ ሲሆን በመላ ሀገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎትም ተቋርጧል።

የእንቅስቃሴ መሪዎች ሰብሰብ ብለው የተቃውሞ ሰልፉን ያቀዱት የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር ለፓርላማየመክፈቻ ንግግር ባደርጉበት በትናንትናው ዕለት እንዲካሄድ ነበር። ሆኖም ትናንት ጁባ ጎዳናዎች ላይ የታየ ጎላ ስብሰባ አልነበረም።

ህዝባዊ ጥምረት ለሲቪል ርምጃ የተባለውቡድን አባል የሆኑት ዋኒ ማይክል ለቪኦኤ የደቡብ ሱዳን ትኩረት ክፍል በሰጡት ቃል የተቃውሞ ሰልፉ ሳይካሄድ የቀረው ከተማዋ ላይ በብዛት ፖሊሶች ተሰማርተው ስለዋሉ "ሰዉ ፈርቶ ሳይወጣ ቀርቷል" ብለዋል።

"የራስህ ዜጎች ስለሀገራቸው ሁኔታማዘናቸውንለመግለጽ ስለወጡ ይህን ያህል ታጥቆ ለማፈን መውጣት ምን ይባላል? ይሄ እኮ በዛሬ የሚቆም ነገር አይደለም፥ ዛሬ ለህዝቡ መንቂያው ቀን ነው፤ ወደፊትም ይቀጥላል " ብለዋል።

ፖሊሶች በበኩላቸው የተቃውሞ ሰልፉን ያዘጋጁት መሪዎች ፈቃድ አልጠየቁም ስለዚህ ችግር የተከሰተ እንደሆን በሚል ኃይሎቻችንን አስማርተናል ብለዋል።

XS
SM
MD
LG