በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ሱዳን ብሄራዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለነገ ተጠርቷል!


ፕሪዚዳንት ሳልቫ ኪር
ፕሪዚዳንት ሳልቫ ኪር

የደቡብ ሱዳን ፖሊስ ነገ ሰኞ በዋና ከተማዋ ጁባ የተጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ ለመመከት በርካታ ፖሊሶችን በከተማዪቱ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ያሰማራ ሲሆን፣ ዜጎችም በመላው አገሪቱ በተጠራው ሰልፍ እንዳይሳተፉ አስጠንቅቋል፡፡

የተቃውሞው ሰልፉ የተጠራበት ምክንያት እንደገና የተዋቀረውና በፕሪዚዳንት ሳልቫ ኪር የሚመራው የሽግግር እና የብሄራዊ አንድነት መንግሥት የደቡብ ሱዳን ዜጎች ለገጠሟቸው በርካታ ችግሮች ተገቢውን መልስ አልሰጡም የሚል እንደሆነ ሰልፉን ያዘጋጀው ቡድን አስታውቋል፡፡

“ሰልፍ ማድረግ ህገመንግስታዊ መብታችን ነው” የሚሉት የአዘጋጆቹ ቡድን አባል አብርሃም አዎሊክ ለቪኦኤ እንደተናገሩት “ዜጎች ሰልፉን ለማድረግ ከማንም ፈቃድ መጠየቅ አያስፈልገንም፣ ልትቃውመው ከምትፈልገው መንግሥት የተቃውሞ ፈቃድ አትጠይቅም” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG