በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሞቃዲሾው ጥቃት ሃያ ዘጠኝ ሰው ሞተ


ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ውስጥ ተስተናጋጅ በሚበዛባቸው ሁለት ምግብ ቤቶች ላይ ትናንት ምሽት ላይ በተፈፀመ ጥቃት ቢያንስ የሃያ ዘጠኝ ሰው ሕይወት ጠፍቷል፡

ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ውስጥ ተስተናጋጅ በሚበዛባቸው ሁለት ምግብ ቤቶች ላይ ትናንት ምሽት ላይ በተፈፀመ ጥቃት ቢያንስ የሃያ ዘጠኝ ሰው ሕይወት ጠፍቷል፡፡

በኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰ ምንም ጉዳት እንደሌለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ አስታውቋል፡፡

ጥቃቱን የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በብርቱ አውግዟል፡፡

ቅዱስ ራማዳን ታጣቂዎቹ የአመፃና የሁከት አድራጎቶቻቸውን ሁሉ የሚያጠናክሩበትና የሚያበዙበት ወቅት እንደሆነ ነው ከልምድ የሚታወቀው፡፡

የትናንት ምሽቱ የሞቃዲሾ ጥቃት ግን ከዚያ በፊት ከተፈፀሙት ሁሉ የከፋና የሰፋ ነበር ተብሏል፡፡

ሞቃዲሾ ሆዳን ወረዳ ውስጥ የምግብ፣ የስፓ፣ የመኝታ፣ ቢሊያርዶና ፑልን የመሣሰሉ መጫወቻወቻዎችና የሺሻ አገልግሎት በሚሰጡት ፖሽ ትሪትስ እና ፒዛ ሃውስ በሚባሉት ሬስቶራንቶች ላይ አልሻባብ ጥቃቱን የፈፀመው በቅድሚያ መኪና ላይ የተጠመደ ፈንጂ ከባድ ጉዳት ካደረሰ በኋላ ስድስት ታጣቂዎች ወደ ቤቶቹ ገብተው በከፈቱት ተኩስ ነው፡፡

ሃያ ዘጠኝ ሰው መገደሉ ተረጋግጧል፡፡ ሃያ ስድስት ሰው ጉዳት ደርሶበት ወደ ሕክምና ተቋማት ተወስዷል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በሞቃዲሾው ጥቃት ሃያ ዘጠኝ ሰው ሞተ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:51 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG