ዋሺንግተን ዲሲ —
የፊታችን ረቡዕ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሚካሄድባት ሶማሊያ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለሕዝብ ተወካዮች በርካታ ገንዘብና እጅግ ውድ ስጦታዎችን እየሰጡ ይገኛሉ ሲሉ የምርጫ ታዛቢዎች ተናገሩ።
ለሁለተኛ የሥልጣን ዘመን የሚወዳደሩት ፕሬዚዳንት ሃሰን ሺሕ አብደላን 23 ዕጩዎች ይቀናቀኗቸዋል።
የሶማሊያ ገለልተኛ የፀረ ሙስና ባለሥልጣን ጉቦ የሚሰጡና የሚቀበሉ አጋልጣለሁ ሲሉ በዛሬው ዕለት አስፈራርተዋል፡፡
ሞሀመድ ኢላድ ሃሰን ያጠናቀረውን ሔኖክ ሰማእግዜር ዝርዝሩን ይዞዋል ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡት::
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ