ዋሺንግተን ዲሲ —
የሶማሊያው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ነገ ረቡዕ ሊካሄድ ቀነ ቀጠሮ ተቆርጦ ቢያዝም የሙስናና ሌሎች ፈተናዎች ክሶች ሳቢያ ለሌላ ጊዜ ተላለፈ።
ለመሆኑ ውሳኔው በጠቅላላው የምርጫ ሂደት ላይ ምን ዓይነት አንድምታ ይኖረው ይሆን?
ወሰብሰብ ባለው የሶማሊያ የምርጫ ሥርዓት መሠረት የተለያዩ የጎሳ እና የየክልል ተወካዮች የሁለቱን ብሔራዊ ምክር ቤቶች ሃምሳ በመቶ አባላት ሲመርጡ፤ ቀሪው የሸንጎ አባላት ተመርጠው ውጤቱ እስኪታወቅ ድረስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫው አይካሄድም።
በሶማሊያ ሕገ-መንግስት መሠረት የአገሪቱ የምክር ቤት አባላት የቀጣዩን የሶማሊያ ፕሬዝዳንት እስኪወስኑ ድረስ ገና ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድ ነው።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡