በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊያ ቸነፈር አስግቷል


ሶማሊያ ውስጥ ይከሰታል ተብሎ የተሰጋውን የበረታ ረሃብ ለማስወገድ ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል።

ሶማሊያ ውስጥ ይከሰታል ተብሎ የተሰጋውን የበረታ ረሃብ ለማስወገድ ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል።

ይሁን እንጂ ሶማሊያ አዲስ መንግሥት እያዋቀረች በመሆኑ የእርዳታው አቅርቦት ለሙስናና ለመንግሥት ጣልቃ ገብነት ሊጋለጥ ይችላል የሚል ሥጋት ተፈጥሯል።

ዘንድሮ ዝናብ በመቅረቱና በመንግሥቱና በአል-ሻባብ ታጣቂዎች መካከል ጦርነቱ በመቀጠሉ በብዙ የሶማሊያ አካባቢዎች ብዙ ሰው ሊራብ እንደሚችል የመንግሥታቱ ድርጅት ተንብይዋል።

እጅግ አጣዳፊ ለሆነ የምግብ እጥረት ይጋለጣሉ የተባሉ 320 ሺኽ ሕፃናትን ጨምሮ ከሕዝቡ አርባ ከመቶ የሚሆነው ወይም 5 ሚሊየን ሶማሊያዊያን እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ድርጅቱ አስታውቋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በሶማሊያ ቸነፈር አስግቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:52 0:00

XS
SM
MD
LG