በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ረሃብና መፈናቀል በፑንትላንድ


ሶማሊያ ውስጥ የተከሰተው ከባድ ድርቅ ቁጥሩ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ ሰው አፈናቅሏል በራስገዟ ፑንትላንድ አርብቶ አደር ማኅበረሰቦች ከብቶቻቸው በዛት በመሞታቸው ወደ አቅራቢያ ከተሞች ተሰድደዋል።

በራስገዟ ፑንትላንድ አርብቶ አደር ማኅበረሰቦች ከብቶቻቸው በዛት በመሞታቸው ወደ አቅራቢያ ከተሞች ተሰድደዋል።

ስደተኞቹን የተቀበሉ ከተሞችም ከዚህ ቀደም በነበራቸው ነዋሪ ላይ ድንገት ብዙ ሰው መታከሉ ጫና ፈጥሮባቸዋል።

ተፈናቃዮቹ ንብረቶቻቸውን በየነበሩባቸው ቀበሌዎች እየጣሉ መውጣታቸውንና በጉዟቸው ወቅትም ብዙ እንግልት የደረሰባቸው መሆኑን አመልክተዋል፡፡

የተፈናቀለው ሰው ቁጥር 430ሽህ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሪፖርት ይናገራል፡፡

ድርቁ ወደለየለት ጠኔና ቸነፈር እንደሚሸጋገር የሰጉ ሶማሊያዊያን በትናንትሽ ከተሞች በሚገኙና አገልግሎት በአግባቡ መስጠት በማይችሉ የመጠለያ ጣቢያዎች ለመኖር

ከሃያ ዓመታት በላይ በጦርነትና በፖለቲካ አለመረጋጋት ውስጥ የቆየችው ሶማሊያ ከነበረችባቸው ሁኔታዎች ለማንሠራራት ጥረት ላይ ብትሆንም ስደተኞች የሚገቡባቸው ከተሞች ከሚኖርባቸው ህዝብ ተጨማሪ ለሚሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሚያጥለቀልቃቸው ሰው የሚበቃ የመሠረተ-ልማት አውታሮች የሌሏቸው መሆኑን ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ረሃብና መፈናቀል በፑንትላንድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:59 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG