በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሎሞን ዴሬሳ አረፈ


ሰሎሞን ዴሬሳ
ሰሎሞን ዴሬሳ

ገጣሚ፣ መምህር፣ የፍልስፍና ሊቅ፣ ጋዜጠኛ ሰሎሞን ዴሬሳ ዛሬ ጥቅምት 23/2010 ዓ.ም. በሰማንያ ዓመት ዕድሜው አረፈ።

ገጣሚ፣ መምህር፣ የፍልስፍና ሊቅ፣ ጋዜጠኛ ሰሎሞን ዴሬሳ ዛሬ ጥቅምት 23/2010 ዓ.ም. በሰማንያ ዓመት ዕድሜው አረፈ።

ሰሎሞን ዴሬሳ የዩናይትድ ስቴትሷ ሚኔሶታ የሚኒያፖሊስ ከተማ ነዋሪ የነበረ ሲሆን ከሥራው ገበታ በብርቱ ሕመም እስከተለየ ድረስ በሚኔሶታ ዩኒቨርሲቲ የሃይማኖቶች ንፅፅር (ኮምፓራቲቭ ረሊጅን) የፍልስፍና መምህር ሆኖ ሲሠራ ቆይቷል።

አቶ ሰሎሞን ዴሬሳ ከሰባት ወራት ህመም በኋላ ዛሬ ያረፈው ልጁ፣ ወንድምና እህቱ፣ ወዳጆቹና ዘመዶችም ሁሉ በተሰበሰቡበት በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ እንደሆነ ታናሽ ወንድሙ አምባሳደር ብርሃኑ ዴሬሳ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

ሰሎሞን ዴሬሳ የተወለደው ከእናቱ ከወይዘሮ የሺመቤት ዴሬሳና ከአባቱ ከአቶ ዳንኪ ላንኪ ወለጋ ጠቅላይ ግዛት ከጊምቢ ስምንት ኪሎ ሜትር ያህል ወጣ ብላ በምትገኝ ጩታ ቀበሌ ነበር።

የሰሎሞን ዴሬሳ አስከሬን የፊታችን ቅዳሜ ከቀትር በኋላ በራሱ ኑዛዜ መሠረት ሚኔፖሊስ ማቃጠያ ኅብረት ሥፍራ እንደሚቃጠል ታውቋል።

ሰሎሞን ዴሬሳ ሦስት መፅሐፎችን አውጥቶ አንባቢ እጅ ይገኛሉ።

ስለአቶ ሰሎሞን ዴሬሣ ሕይወትና ሕልፈት ከታናሽ ወንድሙ ከአምባሳደር ብርሃኑ ዴሬሳ ጋር ዛሬ ያደረግነውን ቃለ ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አምባሳደር ብርሃኑ ዴሬሳ ሰለሰሎሞን ዴሬሳ ለቪኦኤ ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:35 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG