No media source currently available
ገጣሚ፣ መምህር፣ የፍልስፍና ሊቅ፣ ጋዜጠኛ ሰሎሞን ዴሬሳ ዛሬ ጥቅምት 23/2010 ዓ.ም. በሰማንያ ዓመት ዕድሜው አረፈ።ሰሎሞን ዴሬሳ የዩናይትድ ስቴትሷ ሚኔሶታ ነዋሪ የነበረ ሲሆን ከሥራው ገበታ በብርቱ ሕመም እስከተለየ ድረስ በሚኔሶታ ዩኒቨርሲቲ የሃይማኖቶች ንፅፅር (ኮምፓራቲቭ ረሊጅን) የፍልስፍና መምህር ሆኖ ሲሠራ ቆይቷል።