በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ምግብ ፕሮግራም- በአዲስ አበባ


የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚረዱ መሳሪያዎች እና ሌሎች አቅርቦቶች ለሁሉም የአፍሪካ አገራት የሚሰራጩበት ማዕከል በአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የከፈተው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ሥራ መጀመሩን አስታውቋ።
እስካሁንም ከዓለም ጤና ድርጅት የተላኩ መሳርያዎች ለ32 የአፍሪካ ሀገራት፣ ከጃክ ማ ፋውንዴሽን የመጡት ደግሞ ለ48 ሀገራት እየተላኩ መሆኑን ነው ያስታወቀው።
የዓለም የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ስቲቨን ዌር ኦማሞ ለአሜሪካ ድምፅ እንዳስረዱት የግል ንጽሕና መጠበቂዎች ፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ የኮሮና መመርመሪያ መሳሪያዎች እና መተንፈሻዎች ወይም ቬንትሌተሮች እየተሰራጩ ካሉት አቅርቦቶች መካከል ናቸው።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም- በአዲስ አበባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:58 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG