በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን ውጊያ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ600 አሻቀበ


ካርቱም፤ ሱዳን
ካርቱም፤ ሱዳን

በሱዳን ከተቀሰቀሰ ወር ሊኾነው በተቃረበው ከባድ ውጊያ፣ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ600 ማለፉንና የቆሰሉት ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ5ሺሕ500 እንደሚበልጥ፣ የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡

በተደጋጋሚ የተደረሱ የተኩስ አቁም ስምምነቶች፣ ውጊያውን ሊያስቆሙም ኾነ ጋብ ሊያደርጉት አልቻሉም፡፡

የሁለቱ ተፋላሚዎች ማለትም የጦር ሠራዊቱ እና የፈጥኖ ደራሹ ኃይሉ ልዑካን፣ በዋና ከተማዋ ካርቱም እና በሌሎችም ከተሞች፣ በችግር ላይ ለሚገኙ ብዙ መቶ ሺሕ ነዋሪዎች፥ የምግብ፣ የመድኃኒት እና የመጠለያ ርዳታ ለማስገባት የሚያስችል ስምምነት ላይ ለመድረስ፣ ሳዑዲ አረቢያ ጂዳ ላይ መነጋገር ከጀመሩ ቀናት ተቆጥረዋል፡፡

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት፣ 100 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ርዳታ እንደሚሰጥ አስቀድሞ ቃል ገብቷል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የዓለም አቀፍ ፍልሰት ድርጅት(አይኦኤም)፣ በትላንትናው ዕለት እንዳስታወቀው፣ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ፣ ከቀዬአቸው የተፈናቀሉት ሰዎች ቁጥር፣ ከ700 ሺሕ አልፏል፡፡ ሌሎች 100 ሺሕ ሰዎች ወደ ሌላ ሀገር መሰደዳቸውን ድርጅቱ አክሎ አመልክቷል፡፡

አብዛኛው የሰብአዊ ረድኤት እንቅስቃሴ፣ በጸጥታ ችግር የተነሳ ተቋርጧል ወይም በእጅጉ ቀንሷል፡፡

የዓለም የምግብ ፕሮግራም፣ በአገሪቱ ዙሪያ ከሚገኙ የምግብ ማከማቻ መጋዘኖቹ፣ ከ13 እስከ 14 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የምግብ ክምችት መዘረፉን አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG