በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሻሸመኔ ከተማ የሕዝብ ጉባዔ ላይ በደረሰ ሁከት ሶስት ሰዎች ሞቱ፣ 71 ቆሰሉ

ሻሸመኔ ከተማ
ሻሸመኔ ከተማ

በዛሬው ዕለት በሻሸመኔ ከተማ ስቴድየም የተሰናዳ የህዝብ ጉባኤ ላይ በተፈጠረ ሁከት ቢያንስ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 71 ሰዎች መቁሰላቸውን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ።

በዛሬው ዕለት በሻሸመኔ ከተማ ስቴድየም የተሰናዳ የህዝብ ጉባኤ ላይ በተፈጠረ ሁከት ቢያንስ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 71 ሰዎች መቁሰላቸውን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ።

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ-አስኪያጅ ጃዋር መሀመድ በተለያዩ ከተሞች ከህዝብ ጋር የሚያደርገውን ውይይት ይዞ ዛሬ ወደ ሻሸመኔ ያመራ ሲሆን፤ ግጭቱ የተቀሰቀሰው አንድ ፈንጅ ይዟል በሚል ጥርጣሬ ሰው መያዙ ሲሆን፤ ተጠርጣሪው በአስቃቂ ሁኔታ መገደሉን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በስቴድየሙ በደረሰ መገፋፋትና መረጋገጥ የሁለት ሰዎች ህይወት ጠፍቷል፤ 71 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ይላል ፖሊስ ለአሜሪካ ድምጽ የሰጠው መግለጫ።

ፖሊስ የተገኘ ፈንጂ የለም ብሏል። ዘጋቢያችን ሙክታር ጀማል ከአዳማ ተከታዩን አድርሶናል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

በሻሸመኔ ከተማ የሕዝብ ጉባዔ ላይ በደረሰ ሁከት ሶስት ሰዎች ሞቱ፣ 71 ቆሰሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:17 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG