ድሬዳዋ እና ሀዋሳ —
በሻሸመኔና አካባቢዋ ሰላም መሆኑን መንገድም እንዳልተዘጋ፣ አገር አቋራጭ ትራንስፖርትም ከተማዪቱን እያቋረጠው መሆናቸውን ነዋሪዎችና ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል።
“በየቦታው እየተነዙ ያሉ አሉባልታዎች” የሚሏቸው ወሬዎች ግን ከማኅበራዊ ቀውስ በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ጉዳትም እያስከተሉ መሆናቸውን ነዋሪዎቹ ገልጠዋል።
የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “የከተማዪቱ ህዝብ ሰላም ፈላጊ በመሆኑና ከፀጥታ ዘርፍ ጋር በመቀናጀቱ ፀረ-ሰላም እንቅስቃሴ ከሽፏል” ብለዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ በሥጋት ምክንያት በነበረ ጊዜያዊ የትራንስፖርት መቀዛቀዝ በድሬ ዳዋ፣ በሶማሌ ክልልና አጎራባች አካባቢዎች ንግዶች በመጠኑ ቢጎዱም አሁን መደበኛው እንቅስቃሴ መመለሱን ሰውና ሸቀጦችን በማመላለስ ሥራ ላይ የተሠማሩ ሰዎችና ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በየአካባቢው ያሉ ዘጋቢዎቻችን ያጠናቀሯቸውን ዘገባዎች ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።