አዲስ አበባ —
በጉጂ ዞን ሻኪሶ ከተማ የሚገኘው ብቸኛ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ዛሬ ትምህርት መዘጋቱንና አንዳንድ ተማሪዎችም በፀጥታ ኃይሎች መደብደባቸውን የዓይን እማኞች ገለፁ፡፡ ሁኔታው የተፈጠረው ተማሪዎቹ በሞያሌ የተገደሉ ሰዎችን ለማሰብ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት በማጣቱ ነው ብለዋል - እነዚሁ የዓይን እማኞች፡፡
ይሄንን የተመለከተ ምንም ዓይነት ጥያቄ እንዳልቀረበ የገለፁት የከተማዋ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ግን የተደበደበም ይሁን የታሰረ ተማሪ የለም ብለዋል፡፡
እስክንድር ፍሬው ሁለቱንም ወገኖች አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኳል፡፡
-
እስክንድር ፍሬው