በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተራዘመው የሴኔጋል ምርጫ ክረምቱ ከመግባቱ በፊት ይካሄዳል ሲሉ ፕሬዝዳንት ሳል ተናሩ


የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል
የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል

የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ትናንት ሰኞ ለብሔራዊው የምክክር መድረክ ፊት ሲናገሩ ‘የተራዘመው የሃገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ ክረምቱ ከመግባቱ በፊት ይካሄዳል’ ብለዋል። አያይዘውም የስልጣን ዘመናቸው ከሚያበቃበት የሚያዝያ ወር በፊት ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ያላቸውን ቁርጠኝነት ደግመው ገልጠዋል።

ይሁንና ‘የሃገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወሩ መጀመሪያ ላይ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት የምርጫው ቀን በፍጥነት መወሰን አለበት’ ያሉ 16 እጩዎች ግን በብሔራዊ ደረጃ በተጠራው በዚህ የውይይቱ መድረክ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። የሁለተኛ ዙር የስልጣን ዘመናቸውን በማጠናቀቅ ላይ ያሉት ሳል የተፎካካሪዎችን ማንነት አስመልክቶ በተቀሰቅሰው እና አሁንም ድረስ እልባት ባላገኘው ውዝግብ ሳቢያ ምርጫውን ለ10 ወራት ማራዘማቸው ይታወሳል።

ፕሬዝዳንቱ የወሰዱትን እርምጃ ‘ሕገ-ወጥ ነው’ ሲል ውድቅ ያደረገው የሃገሪቱ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት በበኩሉ ባለፈው የካቲት 7/2016 ዓም ባሳለፈው ውሳኔ መንግሥት በተቻለ ፍጥነት አዲስ የምርጫ ቀን እንዲያዘጋጅ ቢያዝም፤ ሳል የሚመሩት መንግስት ግን አሁንም ድረስ ምርጫው የሚካሄድበትን ቀን ቆርጦ ይፋ አላደረገም።

በአንጻሩ ብሄራዊ ውይይቱ በህዝብ እና በፖለቲካ ተዋናዮቹ መካከል የመተማመን ስሜት ለመፍጠር ያለመ ሲሆን፤ የሲቪል ማሕበረሰብ አባላትን እና የሃይማኖት መሪዎችን ያካተተ መሆኑም ታውቋል።

"በትክክልም ውይይት እና ምክክሩ ያስፈለገው ይህን የተዳከመ ሁኔታ እንዲያንሰራራ ለማድረግና ለዲሞክራሲ ያለንን ቀናኢነትን ለማጎልበት ነው" ሲሉ ሳል አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG