በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካጋሜ እንደሚቀጥሉ የታመነበት የሩዋንዳ ምርጫ ተካሄደ


መራጩ ድምፁን መስጠቱን የሚያሳይ ምልክት በጣቱ ላይ እየተደረገ
መራጩ ድምፁን መስጠቱን የሚያሳይ ምልክት በጣቱ ላይ እየተደረገ

በሚሊዮኖች የተቆጠሩ ሩዋንዳዊያን ዛሬ ሰኞ ፕሬዚደንታቸውን እና የምክር ቤት ተወካዮቻቸውን ሲምርጡ ውለዋል፡፡ በምርጫው ህገሪቱን ሰጥ ለጥ አድርገው የሚገዙት ፕሬዚደንት ፖል ካጋሜ ስልጣናቸውን ለተጨማሪ አምስት ዓመት የሚቀጥሉበት እንደሚሆን ይታመናል፡፡

በምርጫው የዘር ፍጅቱ ማብቃቱን ተከትሎ በመሪነት የሚታወቁት እና በኋላም በ2000 ዓም ፕሬዚደንት የሆኑትን ካጋሜን በርካታ ስመ ጥር ተቺዎቻቸው በምርጫው እንዳይካፈሉ በመደረጉ የተፎካከሯቸው ሁለት ዕጩዎች ብቻ ናቸው፡፡

የአሁኑም ፉክክር ከአምስት ዓመት በፊት ከተካሄደው እና ካጋሜ 99 ከመቶውን ድምጽ ካሸነፉበት ምርጫ ጋር ሙሉ በሙሉ ተመሳሳይ በመሆኑ ውጤቱ ምን እንደሚሆን አያጠራጥርም፡፡

በምርጫው ለመወዳደር ማመልከቻ ያስገቡት ስምንት ሰዎች ሲሆኑ የተፈቀደላቸው የዲሞክራቲክ ግሪን ፓርቲው መሪ ፍራንክ ሃቢዜና እና ፓርቲ ሳይወክሉ በግላቸው የሚወዳደሩት ፊልፔ ኢማዪማና ብቻ ናቸው፡፡

ከሩዋንዳ ሕዝብ ስድሳ አምስት ከመቶውን የሚይዙት ከሠላሳ ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች ለአራተኛ የስልጣን ዘመን ከሚወዳደሩት ከካጋሜ ሌላ የሚያውቁት ርዕሰ ብሔር የለም፡፡

የስድሳ ስድስት ዓመቱ ካጋሜ ድህረ የዘር ፍጅት ሩዋንዳን መልሶ በመገንባት ባደረጉት ክንዋኔ ይመሰገናሉ፡፡ በሌላ በኩል አገዛዛቸው ጋዜጠኞችን እና ተቃዋሚዎችን በዘፈቀደ በማሰር በመግደል እና ደብዛ በማጥፋት አፍኖ በመግዛት በመብት ቡድኖች ይከሰሳል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG