በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩዋንዳ ሰኞ ትመርጣለች


የሩዋንዳ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ
የሩዋንዳ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ

ሩዋንዳውያን ሰኞ ምርጫ ሲያካሂዱ የረጅም ጊዜ መሪው ፖል ካጋሜ ምርጫውን በመጠቅለል እንደሚያሸንፉና የአገዛዛቸውን ዘመን እንደሚያራዝሙና በሰፊው በመጠበቅ ላይ ነው።

ካጋሜ ከሰባት ዓመታት በፊት ከገጠሟቸውና ካሸነፏቸው ተፎካካሪዎች ጋራ ለምርጫ እንደሚቀርቡ ሲታወቅ፣ ከእ.አ.አ 1994 የዘር ፍጅት ወዲህ ላለፉት 30 ዓመታት በመሪነት የቆዩት ካጋሜ፣ ከአሳዛኙ ክስተት ወዲህ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲያንሰራራ እና ለበርካታ ዓመታት 7.2 በመቶ ዕድገት እንዲያስመዘግብ አድርገዋል ይባልላቸዋል።

ሆኖም ግን አገዛዛቸው የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን በመደፍጠጥ ሲተች፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ደግሞ የሩዋናዳ ወታደሮች በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ከሚገኙት ኤም 23 አማፂያን ጋራ አብረዋል ሲል ይከሳል።

ባለፉት ሦስት ምርጫዎች ከ 93 በመቶ በላይ ድምጽ ያገኙት ካጋሜ፣ በቅርቡ በተደረገ የሕዝብ አስተያየት መለኪያ መሠረት ደግሞ 99 በመቶ እንደሚያገኙ ይጠበቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG