በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሞስኮው ጥቃት ተሳትፈዋል በተባሉ ላይ ክስ ተመሠረተ


በጥቃቱ በመሳተፍ በሽብር ክስ የተመሰረተባቸው ዳሌርደዘሆን ሚረዞዬቭ፣ ሳኢዳካራሚ ሙሮዳሊ ራቻባሊዞዳ፣ ሻመሰዲን ፋሪዱኒ እና ሞሐማዳሶቢር ዳይዞቭ ናቸው።
በጥቃቱ በመሳተፍ በሽብር ክስ የተመሰረተባቸው ዳሌርደዘሆን ሚረዞዬቭ፣ ሳኢዳካራሚ ሙሮዳሊ ራቻባሊዞዳ፣ ሻመሰዲን ፋሪዱኒ እና ሞሐማዳሶቢር ዳይዞቭ ናቸው።

በሞስኮ አቅራቢያ በመካሄድ ላይ በነበረ አንድ የሙዚቃ ኮንሰርት ወቅት ተኩስ በመክፈት ሰዎችን ገድለዋል የተባሉ አራት ተጠርጣሪዎች ላይ ሩሲያ ትናንት እሁድ ክስ መሥርታለች፡

ተጠርጣሪዎቹ የቀድሞው ሶቪዬት ኅብረት አካል የነበረችው ታጂክስታን ዜጎች የሆኑና በሩሲያ የሚኖሩ ግለሰቦች መሆናቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በምርመራ ወቅት ክፉኛ መደብደባቸውን ያሳያል የተባለ ቪዲዮ በማኅበራዊ ሚዲያ የተለቀቀ ሲሆን፣ ከፍርድ ቤት በወጡ ቪዲዮዎች እና ፍቶ ግራፎች ደግሞ ክፉኛ ቆስለውና ግራ ተጋብተው ተስተውለዋል።

አራቱ ተጠርጣሪዎች በሽብር ወንጀል እንደተከሰሱ እና ከአራቱ ሶስቱ ለቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ እንደሆኑ መግለጻቸውን በሞስኮ የሚገኘው ፍ/ቤት አስታውቋል።

ተጠርጣሪዎቹ የፍርድ ሂደቱ እስከሚካሄድበት ግንቦት ወር ድረስ ተይዘው እንደሚቆዩም ታውቋል።

ጥቃቱን ተከትሎ፣ በሩሲያ የሞት ፍርድ ተግባራዊ በሚሆንበት ሁኔታ ላይ አንዳንድ ሕግ አውጪዎች በመነጋገር ላይ መሆናቸው ታውቋል።

በጥቃቱ እስከ ትናንት እሁድ ድረስ 137 ሰዎች መሞታቸው ሲታወቅ፣ ከመቶ በላይ ደግሞ ቆስለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG