በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሩሲያ የሙዚቃ ድግስ ላይ በተፈፀመ ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 115 ደረሰ


በሞስኮ የሙዚቃ ድግስ ላይ በደረሰው ጥቃት ለተገደሉ ሰዎች መታሰቢያ፣ ክሬሚያ በሚገነው ሲምፈሮፖል የሻማ ማብራት ሥነ-ስርዓት ተካሂዷል - መጋቢት 22፣ 2024
በሞስኮ የሙዚቃ ድግስ ላይ በደረሰው ጥቃት ለተገደሉ ሰዎች መታሰቢያ፣ ክሬሚያ በሚገነው ሲምፈሮፖል የሻማ ማብራት ሥነ-ስርዓት ተካሂዷል - መጋቢት 22፣ 2024

በሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ በተዘጋጀ የሙዚቃ ድግስ ላይ በተፈፀመው እና እስላማዊ መንግስት ሀላፊነቱን በወሰደበት ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 115 የደረሰ ሲሆን፣ ሩሲያ ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ አራት ታጣቂዎችን ጨምሮ፣ በድምሩ 11 ሰዎች ማሰሯን አስታውቃለች።

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጥቃቱ ላይ እስካሁን በይፋ አስተያየት አልሰጡም። ሞስኮ በእስላማዊው መንግስት ኃላፊነት መውሰድ ዙሪያም ምናም ያላለች ሲሆን፣ አንዳንድ የሕግ አውጪዎች ግን ዩክሬን ከጥቃቱ ጋር ግንኙነት ሊኖራት እንደሚችል ጠቁመዋል።

ማንነታቸውን የሚደብቅ ጭምብል ያጠለቁ ታጣቂዎች በሞስኮ ሰሜናዊ ክራስናጎርስክ አካባቢ በሚገኘው የኮርኩስ ከተማ አዳራሽ ውስጥ እየተካሄደ በነበረ የሙዚቃ ድግስ ላይ ጥቃት የከፈቱት አርብ ምሽት ሲሆን፣ በሩሲያ ቢያንስ ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ ያልታየ ከፍተኛ ጥቃት መሆኑ ተገልጿል።

ጥቃት አድራሾቹ ወደ ሩሲያ እና ዩክሬን ድንበር መሸሻቸውን ያስታወቀው የሩሲያ የደህንነት አገልግሎት (ኤፍ ኤስ ቢ)፣ ሀገር ውስጥም 'የሚያስፈልጋቸው ግንኙንት' እንዳላቸው አመልክቷል። አንዳንድ የሩሲያ ሕግ አውጪዎች ደግሞ ያለምንም ማስረጃ ጣታቸውን ወደ ኪየቭ ጠቁመዋል።

የሩሲያ የፓርላማ አባል የሆኑት አንድሬ ካርታፖሎቭ "የዚህ ጥቃት ፍላጎት ያላቸው ምናልባት ዩክሬን እና ደጋፊዎቿ ሊሆኑ ይችላሉ። ይህን ሀሳብ ውድቅ ልናደርገው አንችልም" ብለዋል።

የሩሲያ ባለልስጣናት ድርጊቱ የሽብርተኛ ጥቃት ነው ቢሉም እስላማዊው መንግስት በወሰደው ኃላፊነት ላይ ግን እስካሁን አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG