በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሃያ ሁለቱ ፓርቲዎች ድርድሩን አስመልክቶ ከቀድሞ የፓርላማ አባል ዶ/ር አሸብር ወልደጊወርጊስ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ


የኢትዮጵያው ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግ አስቀድሞ ሃያ አንድ አሁን መድረክ ራሱን ካገለለ በኋላ የሚያካሂዱት ድርድር ጊዜ እና ዕድል የባከነበት ነው ሲሉ አንድ የቀድሞ የፓርላማ አባል ገለጡ፡፡

የኢህአዴግን ፖሊሲዎች ደግፈው የአካባቢው አስተዳደር አፈፃፀም ነቅፈው ዶ/ር አሸብር ወልደጊወርጊስ የፖለቲካ ድርድሩ የዜሮ ድምር ፖለቲካ ሊያጠላበት አይገባምም ብለዋል፡፡

ከድርድሩ ሂደት ትልቁ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ መድረክ በትናንትናው ዕለት ራሱን ያገለለ ሲሆን ስድስት ተቃዋሚ ድርጅቶች አዲስ የመሰረቱት ሌላ ጥምረትም ኢህአዴግ የአደራዳሪ ሚናን አልቀበልም በማለቱ ከድርድሩ ለመውጣት ውይይት እንደሚያደርጉ ገልጠዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG